ኢዜማና ሊቀመንበሩ ኢዜማ ሊቀመንበሩን ዶ/ር ጫኔ ከበደን በትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ ወነጀለ

ሰላም ጤና ይስጥልን በመላው አለም የምትገኙ የተወደዳችሁ የሮሃ ቲቪ ተከታታዮች፣ የመስከረም 21/ 2016 ዓ/ም የረፋድ ዜናዎችን ይዘንላችሁ ቀርበናል።


የአማራ ተወላጆች ወደ አዲስ አበባ እንዳይገቡ የማድረጉ ዘመቻ ተጠናክሮ ቀጥሏል። እነ አቶ ሽመልስና እነ ወ/ሮ አዳነች የኦሮሚያ ልዪ ሃይልን በበተጠንቀቅ አስቁመዋል።

በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ውግያ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

ላሊበላ ፣ ወልዲያ ፣ ደቡብ ጎንደር ምን ተፈጠረ? የሚለውን ይዘናል።

መንግስት ከፋኖ ጋር ለሚያደርገው ውግያ የተገበረው አዲስ ስልት አለ! ፖሊስ አዛዦቹ ተገድለዋል፣ እርስ በርሳቸውም ተዋግተዋል። በዝርዝር እናሰማችኋለን።

ኢዜማ ሊቀመንበሩን ከፋኖ ጋር በሚደረገው የትጥቅ ትግል ተሳታፊ በመሆናቸው መታሰራቸውን በመጠቆም፣ ከፓርቲውም እንዳባረራቸውም አስታውቋል።

የኢትዮጵያን ቀጣይ እጣፈንታ በሚመለከት የተደረገው ጥናት አስፈሪ ሪፖርት ይዞ ወጥቷል።

ኤርትራውያኑ በድጋሜ በእስራኤል ግጭት ውስጥ ገብተዋል፣ የሰው ህይወት አልፏል።

ተመልካቾቻችን አብራችሁን ልትቆዩ ከፈቀዳችሁ እነዚህን መረጃዎች በዝርዝር የምናሰማችሁ ይሆናል፡፡የሮሃ ቲቪ ወቅታዊና ሃቀኛ መረጃዎች እንዲደርሷችሁ ቻናሉን ሰብስክራይብ ፣ ላይክና ሼር በማድረግ አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ።         

ተመልካቾቻችን የሰዓቱ የሮሃ ቲቪ ዜናዎች የተከታተላችኋቸውን ይመስሉ ነበር አብራችሁን ስለነበራችሁ ከልብ ሰላም።

ኢዜማ ሊቀመንበሩን ዶ/ር ጫኔ ከበደን በትጥቅ ትግል እንቅስቃሴ ወነጀለ


የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) የፓርቲውን ፕሬዘዳንት ዶ/ር ጫኔ ከበደን ወንጀለኝነት የሚያረጋግጥ መግለጫ ከፍርድ ቤት ቀድሞ አውጥቷል።

ፓርቲው አጣራሁት ባለው መሰረት" ዶ/ር ጫኔ ከበደ በቁጥጥር ስር የዋሉት በፓርቲያችን ባላቸው ኃላፊነት ሳይሆን በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መሠረት በኮማንድ ፖስቱ ተጠርጥረው ነው" ብሏል።

"ኢዜማ ውስጥ የማይነካም ሆነ የማይተካ አባልም ሆነ አመራር የለም" ያለው ፓርቲው "ስለሆነም ከድርጅቱ ዓላማ እና የትግል መስመር ባፈነገጠ መንገድ በሚንቀሳቀሱ አባላቱ ላይ የፀና አቋም ይይዛል" ሲል ከፍርድ ቤት ቀድሞ ዶ/ር ጫኔን ወንጀለኛ አድርጓል። 

"ከመርሁና እና በግልጽ ካስቀመጠው የሰላማዊ ትግል አቅጣጫ በተለየ መንገድ መጓዝ የፓርቲውን ሕገ ደንብ በግልፅ መጣስ ነው" ያለው ፓርቲ" ከዘመን ዘመን ሲንከባለሉ የመጡ የሃገራችንን የፖለቲካ ችግሮቻችንም ሆነ ህዝባችንን አንገት ያስደፉ እና ለከፋ ድህነት እና ጉስቁልና የዳረጉ ስብራቶቻችንን በማባባስ ሂደት ላይ ከመሳተፍ ተለይቶ አይታይም" ሲል ሊቀመንበሩ የትጥቅ ትግል ውስጥ መሳተፋቸውን ጠቁሟል።

እንግዲህ ይህን ያለው የትጥቅ ትግል ብቸኛው መዳኛ መንገድ ነው በሚል ለአመታት በኤርትራ በርሃ የከረመውን የግንቦት ሰባት ፓርቲ የመሰረቱትና የመሩት የፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ኢዜማ ነው።

የሆነው ሆኖ ግን በማህበራዊ ሚዲያ የዶ/ር ጫኔ ነው በሚል ከፋኖ አባል ጋር ተደርጓል የተባለ የድምፅ ቅጂ ቀድሞ መለቀቁ ይታወቃል።

ይህ ደግሞ በርካታ ሰዎችን ለማሰር ወይም ለመወንጀል ሲፈለግ ቀድሞ የሚተገበር ፋሽን ሆኗል።

ነገር ግን ዶ/ር ጫኔ ከበደ እውን ከፋኖ ጋር ግንኙነት ነበራቸው ወይ?፣ በአማራ ትግል ውስጥስ ዝየተሳተፉ ነው ወይ?፣ የተለቀቀው የድምፅ ቅጂስ የእርሳቸው ነው? የሚሉትንና መሰል ጥያቄዎችን ወይ ከእርሳቸውና ከፋኖ መሪዎች አሊያም ከታሪክ እናረጋግጥ ይሆናል።

አሁን ላይ ግን አመራሮቹንም ሆነ አባላቱን በብልፅግና ውስጥ በመወሸቁ እያጣ ያለው ኢዜማ ቀዳሚ የሊቀመንበሩ ከሳሽና ፈራጅ መሆኑ እያነጋገረ ነው።

በተለይም በደቡብ ጎንደር አካባቢዎች ሚሊሻውን የማሰልጠንና የማሰማራት ተግባሩ ተጀምሯል።

በእብናት ቋሊሳ አካባቢ ከትናንት በስቲያ የተደረገው ውግያም በዚሁ ውሳኔ መሰረት በፖሊስ፣ሚሊሻና በአድማ ብተና ፖሊስ መደረጉ ተሰምቷል።

በውግያውም የፖሊስና የሚሊሻ አዛዦች መገደላቸው ታውቋል።በዚሁ በደቡብ ጎንደር ስማዳ ወረዳ ይኸው መመሪያ ወርዶ ሚሊሻና ፖሊሶች ተዋጉ በመባላቸው አንዋጋምና እንዋጋ በሚሉት መካከል ውግያ ተከፍቶ የአካባቢውን የፖሊስ አዛዥ ጨምሮ በርካቶች ስለመገደላቸው ምንጮች ገልፀዋል።

መከላከያው ተሰላችቷል፣ አካባቢውንም ባለማወቁ ለደፈጠታ ጥቃት እየተዳረገ ነው በሚል ነው አካባቢውን በደምብ ያውቁታል የተባሉት የሚሊሻና የፖሊስ አባላት በውግያው እንዲሳተፉ የተደረገው።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በጎንደርና ዙሪያው በተደረገው ሰሞንኛ ውግያ ውግያውን አልመከቱም በሚል በርካታ የፖሊስ አዛዦች እየታሰሩ መሆኑ ተገልጿል።

የማክሰኚት የፖሊስ አዛዥ፣ በጎንደር ከተማ የሚገኙይ ሶስተኛና ስድስተኛ ፖሊስ ጣቢያ አባላት እንዲሁም ከፋኖ ጋር አንዋጋም ያሉ የወልዲያና የላሊበላ ሚሊሻና ፖሊስ አባላትበመከላከያ ካምፖች እየታሰሩ ነው።

በሰሜን ወሎ ዞን በወልዲያ ከተማ ዙሪያ በትናንትናው እለት ከፍተኛ ተኩስ አንዳለ ሮሀ ከከተማዋ  ነዋሪዎች ሰምታለች።

ነዋሪዎች አያይዘውም በሁሉም አቅጣጫ ማለትም በቃሊም፣ በሳንቃ እንዲሁም በመርሳ ገጠራማ አካባቢዎች ከፍተኛ የተኩስ ድምፅ እንዳለና ውጥረቱ በከተማዋም እንደበረታ ገልፀውልናል።

አማራ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ ሸኖ ላይ የኦሮሚያ ልዩ ሃይል ክልከላ እያደረገ ነው

ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚጓዙ የአማራ ተወላጅ መንገደኞችን ወደ ከተማዋ እንዳይገቡ የሚደረገው ክልከላ ዳግም ተጀምሯል። 

ከተጀመረ ከአንድ ዓመት በላይ ያስቆጠረው  ክልከላው በሰብዓዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶችና በህዝቡ አቤቱታ እንዲቀር ተደርጎ የነበረ ቢሆንም አሁን ድጋሚ ክልከላ እየተደረገ መሆኑን ዋዜማ በስፍራው ተገኝቼ ተመልክቻለሁ ብላለች።

በክልሉ በፋኖ እና በመንግስት መካከል ጦርነት ከተቀሰቀሰ በኋላ፣ ክልከላው  ቀስ በቀስ ዳግም አገርሽቶ አሁን ላይ ተጓዦች ከመንገድ ላይ እንዲመለሱ እየተደረገ መሆኑም ተዘግቧል።

ለጦርነቱ መነሻ ከሆኑ በርካታ የአማራ ህዝብ ጥያቄዎች መካከል ይህ ሰብዓዊ መብትን የጣሰው የብልፅግና የተጠና ክልከላ ነው። ይህንን ክልከላ ሆን ብለው እንደሚፈፅሙ ደግሞ ከንቲባ አዳነችም፣ ጠ/ሚ አብይም በድፍረት በምክር ቤት ውስጥ ተናግረዋል።

የሰሜኑን የኢትዮጵያ ክፍል ከአዲስ አበባ ጋር የሚያገናኘው የደብረ ብረሃን አዲስ አበባ መንገድ የሚያቋርጡ ተጓዞች፣ ሸኖን አልፈው እንዳይሄዱና ወደመጡበት እንዲመለሱ ሲገደዱ በስፍራው የነበረው የዋዜማ ሪፖርተር መመልከቱ በዘገባው ተመላክቷል።

ተሸከርካሪዎችን አስቁመው ከተጓዦች መካከል የአማራ ክልል መታወቂ ያላቸውን ተጓዦች ለይተው ወደመጡበት እንዲመለሱ የሚያስገዱት፣ የየኦሮሚያ ልዩ ኃይልና የታጠቁ ሚሊሺያዎች ናቸው፡፡


0 Comments

Login to join the discussion