መንግስት ከደሴና ከኮምቦልቻ እስረኞችን እያሸሸ ነው! "መከላከያው ወጥቷል" ነዋሪዎች! የጠ/ሚ ዐቢይ ንግግር "በተስፋ አጠግባችኋለሁ!" የሶማሌና ኦሮሞ ጉዳይ!

ሰላም ጤና ይስጥልን በመላው አለም የምትገኙ የተወደዳችሁ የሮሃ ቲቪ ተከታታዮች፣ የመስከረም 22/ 2016 ዓ/ም የምሽት ዜናዎችን ይዘንላችሁ ቀርበናል።


በዋግምኽራ እና በሰሜን ጎንደር  በተከሰተዉ አስከፊ ድርቅ ሰዎች እየሞቱ ነዉ ትሰሙታላችሁ 


የብልፅግና መንግስት በዛሬዉ ዕለት ከአዉሮፓ ህብረት ይለቀቅልኛል ብሎ ሲጠብቀዉ የነበረዉ በጀት መከልከሉን በሚመለከት የያዝነዉ መረጃ አለ


የፓርቲዉ ከፍተኛ አመራር መንግስት ፋኖን እያስታጠቀ ነዉ ሲሉ አነጋጋሪ አስተያየት ሰተዋል በዘገባችን አካተነዋል


በጎንደር ምሽቱን  በራሪ ወረቀት ተበትኖ አድሯል በደሴ እስረኞች ወደ ከሚሴ እየተጓጓዙ ነዉ በኮምቦልቻም ነዳጅ ወደ አዲስ አበባ በከፍተኛ ሁኔታ እየተጫነ ነዉ በቦታዉ ዉጥረት አይሏል። 


ተመልካቾቻችን አብራችሁን ልትቆዩ ከፈቀዳችሁ እነዚህን መረጃዎች በዝርዝር የምናሰማችሁ ይሆናል፡፡የሮሃ ቲቪ ወቅታዊና ሃቀኛ መረጃዎች እንዲደርሷችሁ ቻናሉን ሰብስክራይብ ፣ ላይክና ሼር በማድረግ አሁኑኑ ቤተሰብ ይሁኑ።         

ተመልካቾቻችን የሰዓቱ የሮሃ ቲቪ ዜናዎች የተከታተላችኋቸውን ይመስሉ ነበር አብራችሁን ስለነበራችሁ ከልብ ሰላም።

የኢትዮጵያ መንግስት የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተርን ስም ለማጥፋት ሰነድ አዘጋጅቶ እንደነበር ተሰማ


የኢትዮጵያ መንግሥት በዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም ላይ "ሴራ" ጎንጉኖ እንደነበር መረዳቱን ብሉምበርግ ዘግቧል። 


በዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ የተቀነባበሩትን "የሙስና" እና "የፋይናንስ ወንጀሎች" የሚያሳዩትን የኢትዮጵያ መንግሥት መረጃዎች ከሚስጢራዊ የኢሜል ልውውጦችና ሪፖርቶች በሚስጢር አገኘኹ ያለው፣ በውጭ የሚገኝ አንድ የሚስጢራዊ መረጃ ፈልፋይ ድርጅት ነው። 


በዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ የ"ሙስና" እና "የፋይናንስ ወንጀሎች" መረጃዎችን አቀነባብሯል ተብሎ ስሙ የተጠቀሰው፣ የኢትዮጵያ የፋይናንስ ደኅንነት ተቋም ነው።


የኢትዮጵያ የፋይናንስ ደኅንነት ተቋም በዶ/ር ቴዎድሮስ ላይ ያነጣጠሩ "ሴራዎችን" አቀነባብሮ ነበር የተባለው፣ ዶ/ር ቴዎድሮስ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በጦርነቱ ዙሪያ ተደጋጋሚ መግለጫዎችን ይሰጡ በነበረበትና ለዓለም ጤና ድርጅት በድጋሚ ዋና ዳይሬክተር ኾነው ለመመረጥ ዕጩ በኾኑበት ወቅት እንደነበር ተገልጿል።

ኦነግ ሸኔ በደራ አማራዎች ላይ ማንነት ተኮር ጥቃት መፈፀሙን ተከትሎ ፋኖ ያለልተጠበቀ እርምጃ ወሰደ


አማራ የባለቤትነት ጥያቄ የሚያነሳበትና አሁን በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ስር በሚተዳደረው ደራ ወረዳ ኦነግ ሸኔ ተኩስ ከፍቶ ከ10 በላይ ሰላማዊ ሰዎችን ገድሏል።

በአካባቢው የሚንቀሳቀሰው የኦነግ ሸኔ ታጣቂ ቡድን መስከረም 20/2016 ዓ.ም የአማራ ተወላጆች ላይ ብሔርን መሰረት ያደረገ ጥቃት መፈጸሙን ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

ጥቃቱ የተፈጸመው ከዚህ ቀደምም በተደጋጋሚ ጥቃት በሚፈፀምባቸው በወረዳው የገጠር ቀበሌዎች ነው። 

በመጀመሪያው ቀን ጥቃት ግንደ በርበሬ፣ ቆሮ፣ ራቾ የሚባሉ የገጠር ቀበሌዎች፣ እንዲሁም በሁለተኛው ቀን መስከረም 21/2016  ደግሞ ሰለልኩላና ሳላይሽ የተባሉ የቀበሌ ከተሞች ጥቃት የተካሄደባቸው ቦታዎች ናቸው።

በመጀመሪያ ቀን ጥቃት በሰዎች ላይ ከደረሰው ሞትና ጉዳት በተጨማሪ፣ ተሽከርካሪዎች፣ ቤቶችና የአርሶ አደር ንብረቶች ተቃጥለዋል ተብሏል።

ጥቃቱ ከተፈጸመባቸው ቀበሌዎች መካከል ሳላይሽ በመባል የሚጠራው ቀበሌ አንዱ ሲሆን፣ በአካባቢው በነበረው ግጭት አንድ የአእምሮ ታማሚን ጨምሮ ስድስት ሰዎች መገደላቸውን የቀበሌው ነዋሪዎች ለዋዜማ ራዲዮ ተናግረዋል።

እንዲሁም ሰለልኩላ በሚባለው አካባቢ አራት ሰላማዊ ሰዎች በታጣቂ ቡድኑ ጥቃት መገደላቸውንና ሁለት ሰዎች ቆስለው መጎዳታቸውን ምንጮች ጠቁመዋል። 

በጥቅሉ ከ10 በላይ ሰዎች መገደላቸው የተገለጠ ሲሆን፣ በጥቃቱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ከዚህም ከፍ ሊል እንደሚችል ዋዜማ ከምንጮቿ ተረድታለች።

በተፈፀመው ጥቃት ከሞቱ ሰዎች በላይ የተጎዱት ቁጥር እንደሚጨምርና ተጎጅዎችን በህክምና መርዳት አለመቻሉን በጉንደ መስቀል ከተማ በአንድ የግል ጤና ተቋም የሚሰራ ሀኪም ተናግሯል።

ጥቃቱ የተፈጠረባቸው የገጠር ቀበሌዎች ያለው ሁኔታ አስተማማኝ አይደለም በሚል ተጎጅዎችን ወደ ህክምና ተቋም ማድረስም ይሁን የህክምና ባለሙያዎችን ወደ ቦታው መላክ አስቸጋሪ ሆኗል ተብሏል።

ጥቃቱ የተፈጠረባቸውን ቀበሌዎች ከወረዳው ከተማ ጋር የሚያገናኙ መንገዶች ለተሽከርካሪ ዝግ በመሆናቸው፤ አብዛኛዎቹ ተጎጅዎች ህክምና ለማግኘት መቸገራቸውንም ተናግረዋል። 


በአማራ ክልል በባህርዳርና በደሴ ከተሞች ዙሪያ ውግያ መካሄዱ ሰማ


በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ውግያውና ውጥረቱ ከፍ ያለ ቢሆንም በአንዳንድ አካባቢዎች ግን ተኩሱ ጋብ ማለቱን ተከትሎ መከላከያውና የክልሉ የፀጥታ ሃይሎች የቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ ወጣቱን እያሰሩና እያሰቃዩ መሆኑ ተነግሯል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ወጣቱ ቤቱን ጥሎ ከፋኖ ጋር ለመቀላቀል ወደ ጫካ እያመራ መሆኑ ታውቋል።

በክልሉ ርእሰ መዲና ባህርዳር ከሰሞኑ የደፈጣ ጥቃቶች ሲደረጉ እንደነበር ይታወቃል።

በትናንትናው እለትም በባህርዳር ሳባታሚት ማረሚያ ቤት አቅራቢያ ጎርድማ ገብርኤል ተብሎ በሚጠራው አካባቢ የቤት ለቤት አሰሳ በማድረግ ትጥቅ ለማስፈታት በመሞከሩ  ውግያ መከፈቱ ተነግሯል።

መከላከያውን ጨምሮ የክልሉ ፀጥታ ሃይሎች አርሶ አደሩ ያስመዘገባቸውን ህጋዊ መሳሪያዎችን እየዞሩ መልቀም ጀመሩ ይላሉ ነዋሪዎች።

ነገር ግን በዚህ ያልተስማሙት በከተማዋ ዙሪያ የሚገኙ አርሶ አደሮች መሳሪያቸውን እየወለወሉ ውግያ ገጠሙ ይላሉ።

ከዚያ በኋላም ለ2 ሰዓታት የዘለቀ ተኩስ መከላከያው ከአርሶ አደሩ ጋር በባህርዳር ዙሪያ አደረገ ብለዋል።

ተኩሱ ባህርዳር መሀላ ከተማ ድረስ ይሰማ እንደነበርና በርካታ አርሶ አደሮች እንደቆሰሉ፣ እንዲሁም የፖሊስ አዛዡን ጨምሮ በርካታ ፖሊሶችም ጉዳት አስተናግደዋል።


በጎንደር እና አካባቢው የተለያዩ መልዕክቶች የያዙ ወረቀቶች መበተናቸው  ተሰማ


ትላንት ሌሊቱን ማለትም መስከረም21/2016 ዓ/ም ከጎንደር  እስከ ማክሰኝት ባሉ አካባቢዎች የተለያዩ መልዕክቶች የያዙ ወረቀቶች ሲበተኑ ማደራቸው ተነግሯል።


በተበተኑት በራሪ ወረቀቶች ላይም  ማንኛውም ሰው ከህልዉና ትግሉ ጎን እንዲቆም ፣ አሉባልታ የሚነዙ ሰወች ላይ እርምጃ እንደሚወሰድ ፣የገበያ እና የፍጆታ ምርቶችን የሚደብቁ ነጋዴዎች ላይም ተመሳሳይ እርምጃ እንደሚወሰድ እንዲሁም የህዝብን ነፃነት ትግል የሚያደናቅፍ የፋኖን እንቅስቃሴ በመሰለል መረጃ አሳልፎ የሚሰጥ እና በፋኖ ስም ዝርፊያ የሚፈፅሙ አካላት ከድርጊታቸው እንዲቆጠቡ እናሳስባለን የሚሉ እና በርካታ መልክቶች መተላለፋቸውን ኢትዮ ኒዉስ ዘግቧል።



0 Comments

Login to join the discussion