ብልፅግና በፋኖ ምክንያት ያፈሰሰው ረብጣ ብር! አቶ አገኘሁ "ተዘጋጅተናል!" አሉ! ለጠ/ሚሩ ጥያቄ አናቀርብ ያሉት የፓርላማ አባላት! የቦሌ ቡልቡላው ተኩስ! ክርስቲያን ታደለ አብይ አህመድ ምሬ ወዳጆ ፓርላማው

የአብይና የኢሳያስ ፎቶዎች

ዜና 7

ኤርትራ ኢሳያስ አፈወርቂና ዐቢይ አህመድ የተነሷቸውን ፎቶዎች ማስወገዷ እያነጋገረ ነው



የኤርትራው የማስታወቂያ ሚንስትር አቶ የማነ ገብረመስቀል  ከሀምሌ 2/2010 ጀምሮ ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ፕሬዝደንት ኢሳያስ አፈወርቂ ሲገናኙ በቲውተር ገፃቸው የተለጠፉ ፎቶዎችን ከትናንት በስቲያ ጀምሮ አጥፍተዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩና ፕሬዝደንቱ በሳውዲ ሪያድ በነበራቸው ቆይታ ፊት ለፊት ተገናኝተው አለመወያየታቸው ተሰምቷል።

በዚህ ሁኔታ ሁለቱ መሪዎች በአንድ ወቅት ከነበራቸው የጠበቀ ግንኙነት ወጥተው ወደ ከረረ ፀብ ውስጥ መግባታቸው እየተመላከተ ነው።

ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላ ወደ የለየለት ፀብ ገብተዋል የሚባሉት ሁለቱ መሪዎች አሁን ለውግያ የሚፈላለጉ ሆነዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ የቀይ ባህርን ጉዳይ አንስተው ወደ ውግያ ለማምራት እያሟሟቁ መሆኑም ተስተውሏል።

ኢሳያስ በበኩላቸው ቀይ ባህርን አብረን እንጠብቅ ሲሉ ለቀጠናው አገራት ጥሪ አድርገዋል።

ሁለቱም አገራት በድንበር አካባቢ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑንም አለም አቀፍ ሚዲያዎች ጭምር እየዘገቡ ነው።

የቀጠለው እገታ

ዜና 4

በአርሲ ዞን አሰላ ከተማ ዙሪያ ያሉ ነዋሪዎች በሚፈፀምባቸው እገታ ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ገለፁ


በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በተለይም አሰላ ከተማ ዙሪያ ላይ ያሉ ነዋሪዎች እየተባባሰ የመጣዉ የእገታ ወንጀል እንዳማረራቸው ተናግረዋል።

ነዋሪዎቹ "ሰዎችን አግቶ ከፍተኛ መጠን ያለዉ ገንዘብ የመጠየቅ ተግባር ህብረተሰቡን አማሯል" ይላሉ።

ከአሰላ ከተማ በቅርብ ርቀት ላይ በሚገኙ ገጠራማ ቀበሌያት፤ በተለይም ሄጦሳ ወረዳ፤ ቂሊሳ በሚባል አከባቢ በሌሊት ሰዎችን በማገት ገንዘብ መጠየቅ እየተለመደ የመጣ ተግባር ሆኗል ሲሉም ነው የሚገልፁት። 

ይህ ቦታ ቁሉምሳ ከሚባለው የአሰላ ከተማ መግቢያ አከባቢ እጅግ ቅርብ ርቀት ላይ የሚገኝ መሆኑንም ነዋሪዎች ጠቅሰዋል።

በዶዶታም ተመሳሳይ የእገታ ተግባር በሌሊት ይፈፅማል የሚሉት ነዋሪዎቹ ከከተማ ውጪ ያለው የትኛውም አከባቢ መሰል ስጋት አለበት ይላሉ፡፡ 

ሰዎች ሲታገቱ ባላቸው የኢኮኖሚ አቅም የተለያየ መጠን ያለው ገንዘብ እንዲከፍሉ በአጋቾቻው ይወሰንባቸዋል።

የታገቱት ሰዎች የተጠየቁትን ተደራድረው ከፍለው ከመውጣት ውጪ ህይወታቸውን የማቆያ ሌላ ስልት እንደሌላቸውም ነው የሚጠቅሱት።

በዚህም ቀላል የማይባል ቁጥር ያላቸው አርሶ አደሮች አከባቢውን ለቀው ወደ ከተማ በመሸሽ ላይ ሲሆኑ አቅም የሌለው ግን አከባቢው ላይ ተቀምጦ የሰቀቀን ህይወት ይመራል ሲሉ ገልፀዋል።

የብልፅግና ዶክመንተሪ

ዜና 3

ብልፅግና "የፋኖን ስም ያጠለሽልኛል" ያለውን ዶክመንተሪ እያሰራ መሆኑ ተሰማ


 በሰሜን ወሎ ዞን ራያ ቆቦ ከተማ የብልፅግና መንግስት የፋኖን ስም ለማጠልሸት ዶክመንተሪና የዜና ዘገባ እየሰራ መሆኑ ታውቋል።

ዶክመንተሪውንና ዘገባውን እየሰራ ያለውም በራያ ቆቦ ኮርማት ወንዝ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑ ተሰምቷል።

ይህ ዘገባና ዶክመንተሪ በኢቢሲ፣ በፋና ፣ በዋልታ፣ በአሚኮ ፣በአዲስ ቲቪና በመሰል የመንግስት ልሳን የሚዲያ ባለሞያዎች እየተዘጋጀ ሲሆን ፣ ከፍተኛ በጀት እንደተበጀተለትም ለማወቅ ተችሏል።

የዚህ ዶክመንተሪ አላማም ፋኖ ዝርፊያ፣ ግድያና አስገድዶ መድፈርን እንደሚፈፅም እንዲሁም ህዝቡ እንደሚማረርበት ለማመልከት ነው ተብሏል።

ይህም ኢሰመኮን ጨምሮ የተለያዩ የአገር ውስጥና የውጭ  ሚዲያዎችና ተቋማት የብልፅግና ጦር በንፁሃን ላይ የሚፈፅመውን ግድያ፣ አስገድዶ መድፈርና ዝርፊያ በማጋለጣቸው የመልስ ምት ለመስጠት ያለመ ነው የሚል መረጃ ወጥቷል።

በተጨማሪም የፋኖ ሃሎች ያላቸውን ህዝባዊ ቅቡልነት ለመንጠቅ ያለመ ነው።

ይሁን እንጂ ፋኖ ራሱ አርሶ አደሩ፣ ተማሪውና መምህሩ፣ ነጋዴውና ወጣቱ በመሆኑ ዶክመንተሪው የሚነገረው ለማን እንደሆነ ግራ ያጋባል ይላሉ ያናገርናቸው አስተያየት ሰጪዎች።

በዚህ ዶክመንተሪ የራያ ቆቦ ነዋሪዎች "አንሳተፍም ፣ ያልተደረገን ነገር አናወራም" በማለታቸውም ብዙዎች ታፍነው ተወስደዋል።

በመሆኑም በጎዳና ላይ ያሉ፣ በሴተኛ አዳሪነት የሚተዳደሩ ፣ እንዲሁም የሚሊሻ ሚስቶችን በማስፈራራትና በገንዘብ በመደለል ዶክመንተሪው እየተሰራ መሆኑ ታውቋል።

በዚህ ዘገባና ዶክመንተሪ ላይ የሚተውኑ ህፃናት ፣ ነብሰ ጡር ሴቶች ፣ ሴተኛ አዳሪዎችና አዛውንቶች ጭምር ያሉበት ሲሆን ዳጎስ ያለ ገንዘብ እንደሚሰጣቸውም ቃለ ተገብቶላቸዋል።

በአካባቢው ያለው ማህበረሰብም ይህን ተግባር በመረዳት ቁጣውን እያሰማ ነው።

0 Comments

Login to join the discussion