የጥር 17 የረፋድ ዜና

  • የሶማሌ ላንዱ ፕሬዘዳንት ሙሴ ቢሂ የብልጽግና ሰዎችን ውሸት አጋልጠዋል፡፡ የወደብ ኪራዩ ለምን አላማ እንደሚውልም በይፋ ተናግረዋል፡፡
  • ከወለጋ ጭፍጨፋ አምልተው በአማራ ክልል የተጠለሉ ተፈናቃዮችን ዳግም ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ ተሰማ፡፡
  • አማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ውጊያ ቀጥሏል፡፡ በሰሚነ ወሎ የምስራቅ አማራ ፋኖ ታላቅ ጀብዱ ፈጽሟል፡፡
  • በንጹሃን ደም እጃቸው የታጠበውን ጠቅላይ ሚኒስትር የባረኩና የመረቁት ጳጳስ ጉዳይ እያነጋገረ ነው፡፡ጳጳሱ ስራዬ አብይን መባረክና መመርቅ ነው እያሉ ነው፡፡፡

  • የተከበበው የአገዛዙ ጦር

የምስራቅ አማራ ፋኖ በተኩለሽ የሚገኘውን ከፍተኛ የአገዛዙን ሃይል ከበባ ውስጥ ማስገባቱን አስታወቀ ከሰሞኑ የዐቢይ አህመድ ጦር ሳያስበውና ሳያልመው በሰሜን ወሎ ራያ ቆቦ የምስራቅ አማራ ፋኖዎች ከላይ እሳት ከታች እሳት እያነደዱበት ነው፡፡የጥይቱ እሳት እየለበለበው ፣ የባሩዱ ጭስ እያፈነውም መግቢያ መውጪያ አጥቷል፡፡ የምስራቅ አማራ ፋኖ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ አበበ ፈንታው ከሰሞኑ በአገዛዙ ሰራዊት ላይ ስላደረሱት ኪሳራ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡ ጠንካራ ነው የተባለውን በተኩለሽ የሰፈረውን ጦር ከበባ ውስጥ በማስገባት ደምሠነዋል ብለዋል ለአማራ ድምጽ በሰጡት አስተያየት፡፡ፋኖ አበበ ሰራዊቱ ላይ ከበባ በመፈጸም መውጪያ እንዳያገኝ አድርገናል ያሉ ሲሆን ፣ በርካታ መሳሪያ ማርከን ሰራዊታችንን እያስታጠቅን ነው ብለዋል፡፡በራያ ቆቦ ካሉ ከ44 በላይ ቀበሌዎች ውስጥ ከጥቂቶቹ ውጪ አብዛኛዎቹ በፋኖ እጅ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህም የአገዛዙ ሃይል በአስፋልት መንገድ ላይ ከሚገኙት እንደጎብዬና አራዶምን በመሳሰሉ አካባቢዎች ይንቀሳቀሳል እንጂ በሌሎች አካባቢዎች ያለነው እኛ ነን ብለዋል፡፡


  • የወለጋ ተፈናቃዮችና የመመለስ አጀንዳ

የአማራ ብልጽግና ሰዎች በድጋሜ ተፈናቃይ አማራዎችን ወደ ወለጋ እንመልሳለን ሲሉ ተደመጡ ደም እንደጎርፍ በወረደበት ፣ የንጹሃን አማራዎች ሆድ በካራ በተቀደደበት፣ "ወላሂ ሁለተኛ አማራ አልሆንም" በተባለበት የምዕራብ ወለጋ ቶሌ ቀበሌ አሁንም ከፍተኛ ስጋቶች አሉ፡፡ታዲያ ሆድ አደርና ተላላኪነት የየእለት ግብራቸው የሆነው የአማራ ብልጽግና ሰዎች በማይስተዳድሩት የአማራም የኦሮሚያም ክልል ጉዳይ እየገቡ ተፈናቃይ ካልመለስን እያሉ ነው፡፡በምዕራብ ወለጋ ጊምቢ ወረዳ ቶሌ ቀበሌ በሺህ የሚቆጠሩ ቤተሰቦቻቸው በጭካኔ ተጨፍጭፈው ያለቁባቸው ንጹሃን አማሮች ዛሬ ላይ ከሰፈሩባቸው የወሎ አካባቢዎች ወደ ወለጋ ተመልሳችሁ እንደፍጥርጥራችሁ ሁኑ እንጂ እዚህ ቦታ የላችሁም እየትባሉ ነው፡፡፡

የአሜሪካ ድምጽ እነዚህን ተፈናቃዮችን ወደ ቀዬአቸው ለመመለስ ዝግጅት እንደተደረገ የአማራ ብልጽግና ማስታወቁን ዘግቧል፡፡የእነ አረጋ ከበደ ቡድን ምክትል ቃል አቀባይ ነው የተባለው ወንደወሰን ለገሰ፤ "በምሥራቅ እና ምዕራብ ወለጋ ዞኖች ከሚገኙ ስድስት ወረዳዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች ተመሳሳይ ዝግጅት እየተደረገ ነው" ሲል ተደምጧል፡፡በወለጋ ዞኖች ያሉ የዞን ፣ የወረዳና የቀበሌ አመራሮች በአማራ ክልል ያሉ ተፈናቃዮችን ለመቀበል ምንም ዝግጅት እያደረጉ እንዳልሆነ እየገለጹ ነው፡፡በወለጋ አካባቢዎች በአሁኑ ሰዓትም የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በስፋት እየተንቀሳቀሱና ዛቻም ጭምር እያሰሙ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡በሰሜን ወሎ ዞን ሐርቡ መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ አንዳንድ የኦሮሚያ ክልል ተፈናቃዮች ግን፣ በቀድሞ ቀዬአቸው የጸጥታ ሁኔታ መሻሻል ላይ እንዳልሆነ ይናገራሉ፡፡ከዚህ ቀደም ሮሃ ያነጋገረቻቸው ትመለሳላችሁ የተባሉ ተፈናቃዮችም በአካባቢው የቀሩ ሰዎች እንደነገሯቸው ጠቅሰው አሁንም የወለጋ አካባቢዎች የሞት ጥላ ያጠላባቸው ስፍራዎች መሆናቸውን ተናግረው ነበር፡፡

  • አብይን የባረኩት ጳጳስ

ንጹሃንን እየጨፈጨፈ ያለውን መከላከያን እና ሃገርን በጦርነት እያመሱ ያሉትን መሪ የባረኩት ጳጳስ ጉዳይ እያነጋገረ ነው ዐቢይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመጡ ማግስት ጀምሮ በኢትዮጵያ ምድር ላይ ታሪክ አይቶት የማያውቀውን ጦርነትና ፍጅት አስተናግደዋል፡፡ሚሊዮኖች በጦርነት ፣ 10 ሺዎች በማንነት ጥቃት አልቀዋል ፣ 10 ሚሊዮኖች ደግሞ በርሃብ አለንጋ እየተገረፉ ነው፡፡ አገር የመፈረስ አፋፍ ላይ ደርሳለች፣ ህዝብ የመበትን አደጋ ተጋርጦበታል ፣ ወጥቶ መግባት በልቶ ማደር አዳጋች ሆኖበታል፡፡ታዲያ በዚህ ሁሉ መሃል የእምነት ተቋማትና አብዛኛዎች የሃይማኖት አባቶች ከሃገርና ከምዕመናቸው ደህንነት በላይ ስልጣንና ምቾታቸውን አስቀድመው ፣ ከፈጣሪያቸው ይልቅ መንግስትን ፈርተውና ታዘው ታይተዋል፡፡ነገር ግን የህዝባቸው መከራ የታያቸው ፣ ቁስሉ ያመማቸው ፣ ሞቱ ያስጨነቃቸው እንደ አቡነ ሉቃስ ያሉ ጳጳሳት ሞት ይቁም፣ ግፍ ይብቃ ሲሉ ድምጻቸውን አሰምተዋል፡፡ ለዚህ ሁሉ መከራ የዳረገውን ሰይጣናዊ መሪም አውግዘዋል፡፡ከዚህ በተቃራኒ ደግሞ ለሆዳቸው ያደሩ ፣ ምዕመናቸውን የዘነጉ ፣ በዐቢይ አህመድ ሽንገላና ሙገሳ የተደለሉ አስኬማ ጫኝ ጳጳሳት የራሳቸው ምቾት ስላልተነካ ጠቅላዩን ቅዱስ ፣ አውጋዣቸውን እርኩስ አድርገው ቀርበዋል፡፡በዚህም አቡነ ሩፋኤል የተባሉ የሲኖዶሱ አባል ጳጳስ በሀገረ ስብከታቸው ጋምቤላ ሌሎች ጳጳሳትን ሰብስበው እጃቸው በደም የታጠበውን ዐቢይ አህመድን ሲመርቁና ሲባርኩ ተሰምተዋል፡፡ይህም በአብዛኛው ምዕመን ዘንድ ቁጣን ቀስቅሷል፡፡

  • ሶማሌላንድ ያጋለጠችው የብልጽግና ውሸት

ሶማሌላንድ ለኢትዮጵያ ያከራየሁት ወደብ ለንግድ አገልግሎት አይውልም ስትል አጋለጠች በቅጥፈትና በማታለል የሚታወቁት ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ የኢትዮጵያን ህዝብ ወደብ አስገኘውልህ ፣ ካሁን በኋላ ኑሮህ ቀለለ ሲሉ ሊደልሉት ሞክረዋል፡፡ምንም እንኳን በጦርነትና በኑሮ ውድነት ደቁሰውት አንቅሮ የተፋቸው ህዝብ ይህን የሚሰማበት ጆሮ ባይኖረውም፡፡ታዲያ ከሬድዋን ሁሴን እስከ ምስጋኑ አረጋ ፤ ከፋና እስከ ኢቢሲ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር  ተስማምታ የወደብ ባለቤት ሆነች ፣ ወደቡንም ለወታደራዊ አላማና ለንግድ ትጠቀምበታለች ሲሉ ነጭ ውሸት ዋችተዋል፡፡የሶማሊላንድ ፕሬዝዳንት ሙሴ ቢሂ ግን ከኢትዮጵያ ጋር የተፈረመው የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት የባሕር ኃይል ጣቢያ ማቋቋምን እንጂ አዲስ የወደብ አገልግሎትን አይመለከትም በማለት በስምምነቱ ዙሪያ በሰጡት ማብራሪያ ተናግረዋል። ለኢትዮጵያ የሚሰጣት የባሕር ኃይል ጦር ሠፈር ለወታደራዊ ዓላማ ብቻ እንደሚውል የገለጡት ቢሂ፣ ሸቀጦችን ለማጓጓዝ ተግባር እንደማይውልና ኢትዮጵያ ለወጪና ገቢ ንግዷ በርበራ ወደብን ብቻ እንደምትጠቀም ተናግረዋል። ፕሬዝዳንቱ የመጨረሻው ስምምነት ሲፈረም፣ ኢትዮጵያ ለሶማሊላንድ የአገርነት እውቅና መስጠቷ በይፋ ይገለጣል ብለዋል።

0 Comments

Login to join the discussion