ከጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ሞት ጋር በተያያዘ አዳዲስ መረጃዎች አየወጡ ነው

ከቀናት በፊት ህይወቱ ያለፈው ጋዜጠኛ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) የሞተው ራሱን አጥፍቶ ነው የሚል መረጃ ወጣ

ባሳለፍነው ሳምንት ህይወቱ ያለፈው ጋዜጠኘ ገነነ መኩሪያ (ሊብሮ) ራሱን በገመድ አንቆ ህይወቱን እንዳጠፋ ኢትዮጲካሊንክ  የሬዲዮ ኘሮግራም ዘግቧል።የዛሬ 6 ወር ገደማ በስኳር ህመም ምክንያት አንድ እግሩን መቆረጡን ያነሳው ዘገባው፣ ከዛ በኅላ ህይወት እንዳስጠላውና ወዲህ ወዲያ ሲል ባለቤቱ መኪና እየነዳች እንደምታደርሰው ገልጿል፡፡
አንድ ቀን ግን ባለቤቱን ግዬን ሆቴል ስራ አለብኝ አድርሺኝ ብሏት አድርሳው ወደ ቤት ብትመለስም እሱ ግን ወደ ሌላ ቦታ በመሄድ ስልኩን በማጥፋት ሆቴል ይዞ ተደብቆ ትንሽ ቀናትን ቆይቷል ሲልም ያክላል::ብቻውን እዛ ክፍል ውስጥ የከረመው ጋዜጠኛ ገነነ  ምን እንደሆነ  ለምን እዚዚህ ውሳኔ ላይ እነደደረሰ ባይታወቅም ራሱን በገመድ አንቆ እንደገለ በምርምራ ታውቋል ብሏል።"ባለቤቱ ሞቱን ስትሰማ ወደ አረፈበት ሆቴል በመሄድ ለፖሊስ መናገርና ማሳወቅ ሲገባት ሬሳውን ወደ ቤቷ አምጥታ ስታለቅስ የጎረቤት ሰዎች ለፖሊስ አመልክቺ እንጂ ብለው ሲጠይቋት ለፖሊስ ያመለከተች ሲሆን ፖሊስም እንዴት የሞተ ሰውን አስክሬን ለፖሊስ መናገርና ማሳወቅ ሲጋባሽ አስክሬኑን ይዘሽ ወደ መኖሪያ ቤትሽ ትሄጃለሽ ብሎ አንድ ቀን እስር ቤት አውሏት ነበር" ሲል ኢትዮፒካልንግ በዘገባው አመልክቷል፡፡ሮሃ ስለጉዳይ ከቤተሰቦቹ ለማጣራታ ያደረገችው ሙከራ ለጊዜው አልተሳካም፡፡

0 Comments

Login to join the discussion