ጋዜጠኛ ናትናኤል ያለምዘውድ ከግፍ እስር ተፈታ

ብልጽግና አፍኖት የከረመው ናትናኤል ያለምዘውድ ከግፍ እስር ተፈታ

ከታህሳስ 10/2016 ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ወር ከአስር ቀናት ገደማ ‹‹በኦህዴድ-ብልፅግና ሀይሎች ታፍኖ በግፍ እስር ላይ የነበረው፣ የባልደራስ ፓርቲ የወጣቶች ዘርፍ ኃላፊ እና የስራ አስፈፃሚ አባል የሆነው ናትናኤል ያለምዘውድ ዛሬ በ40 ሺህ ብር ዋስ ተፈቷል።›› ሲል ባልደራስ አስታውቋል፡፡
አዲስ አበቤው ናትናኤል ከዚህ ቀድም ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት የግፍ እስረኛው ያለ አግባብ 14 ተጨማሪ ቀናት እንደተሰጠበት መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን የአቶ ናትናኤል ያለምዘውድ ጠበቃ በጥር 15/2016 ዓ.ም ለከፍተኛው ፍርድ ቤት ይግባኝ ብለው ነበር።
በዚህም መሰረት ፍርድ ቤቱ አርብ ጥር 17/2016 ዓ.ም በዋለው ችልት የግፍ እስረኛው በ40 ሺህ ብር እንዲወጣ ወስኖለት የነበረ ቢሆንም የዋስ ብሩን ካስያዘ በኋልም ለ4 ቀናት ሳይፈታ እንዲቆይ ተደርጓል፡፡ያም ሆኖ ግን ዛሬ ዕለተ ሰኞ ናትናኤል ያለምዘውድ ከወር በላይ ከቆየበት የግፍ እስር ተፈቶ ከቤተሰቦቹ ጋር መገናኘቱን ሮሃ ከቅርብ ሰዎች ማረጋገጥ ችላለች፡፡

0 Comments

Login to join the discussion