የፋኖ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አስረስ ማረ ስለ ድርድር ጉዳይ ተናገሩ


ህዝባችንን ከሚደርስበት ጭፍጨፋ ነጻ ሳናወጣ በድርድር ጉዳይ አስተያየት አንሰጥም ሲል ፋኖ አስታወቀ

የአማራ ህዝባዊ ሃይል ፋኖ የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ፋኖ ጠበቃ አስረስ ማረ ዳምጤ ከሰሞኑ አደረጃጀታቸው ባወጣው መግለጫ ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡የትራንስፖርት እንቅስቃሴን በሚመለከት ባደረጉት የእንቅስቃሴ ፍቃድ ላይ በሰጡት ምላሽም "ፈቃዱ የተሰጠው የአማራን ህዝብ የሚያማርር ነገርን ማስቀረት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ ነው" ብለዋል፡፡"በዋናነት እየታዋጋን ያለው መከላከያ የሚባለው ሰራዊት ነው" የሚሉት ፋኖ አስረስ "ነገር ግን አገዛዙ ለቀድሞ ልዩ ሃይል አባላት የዳግም ስልጠና ጥሪ እያደረገ በመሆኑ በዚህም ላይ ማሳሰቢያ ሰጥተናል" ሲሉ ገልጸዋል፡፡
ፋኖ አስረስ ስርዓቱ በየጊዜው ስለድርድር ቢያወራም መሬት ላይ ባለው ሁኔታ ግን የአማራን ህዝብ እየጨፈጨፈ ነው ይላሉ፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ የህዝብችንን ጭፍጨፋ ሳናስቆምና የህዝባችንን ነጻነት ሳናረጋግጥ ስለድርድር ለማውራት ሃሳብ የለንም ፣ ጊዜውም አይደለም ሲሉ ተናግረዋል፡፡ህዝባችንም ከእረኛ እስከ ምሁር ፣ ከነጋዴ እስከ ገበሬ ጦርነቱን ቶሎ በድል ጨርሱ ይለናል እንጅ የአገዛዙን የከሃዲነት ባህሪ ስለሚያውቀው ተደራደሩ እያለን አይደለም ይላሉ፡፡
በጎጃም መርዓዊና አካባቢው የሚንቀሳቀሰው የኮለኔል ታደሰ ሙሉነህ ብርጌድ ከትናንት ጠዋት 11 ሰዓት ጀምሮ ከአገዛዙ ሃይል ጋር ውጊያ አድርጓል ብለዋል፡፡ፋኖ  በአገዛዙ ላይ ከባድ ኪሳራ በማድረሱም የብልጽግና ጦር በንጹሃን ላይ ጭፍጨፋ ፈጽሟል ብሏል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion