የብልፅግና ባለስልጣናት ስለድርድር አስተያየት መስጠት ጀምረዋል።


ከፋኖ ጋር ለመደራደር ዝግጁ ነኝ ያለው ብልጽግና ጦርነቱን ግን ለአንድ ደቂቃም ቢሆን ማቆም አልፈልግም አለ

ሰላም ፋለጊ ለመመስል በእየሚዲያዎቹ ፕሮፓጋንዳውን የሚያስነግረው ብልጽግና መደራደር እፈልጋለሁ ግን ጦርነቱን ለአንድ ደቂቃም ቢሆን ማቆም አልፈልግም ማለቱ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡
ትናንት መግለጫ የሰጡት የዐቢይ አህመድ ስልጣን አስጠባቂ የብአዴን ባለስልጣናት በሉ የተባሉትን ተናግረዋል፡፡
የአረጋ ከበደ ጓደኛ የሆኑት የክልሉ ሰላምና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ነኝ የሚሉት አቶ ደሳለኝ ጣሰው ሰሞኑን አቶ ደመቀ መኮንን በተሰናበቱበት የብልጽግና ስብሰባ ላይ ድርድር ለማድግ አቅጣጫ አስቀምጠናል ካሉ በኋላ ጦርነቱን ግን ለአንድ ደቂቃም ቢሆን አናቆምም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
ደሳለኝ ጣሰው እርስ በርሱ የሚጣረስ ንግግር ባደረጉበት መግለጫ አገዛዙ ምን ያህል ውዝግብ ውስጥ እንዳለ የሚጠቁም ምልክት ሰጥተዋል፡፡
ሰውየው በመግለጫው አክለውም ለቅጥረኛ የፖሊስና ሚሊሻ አባላት ስልጠና በተሰጠበት ወቅት የአማራን ህዝብ ማወረዳችንን አምነናል ያሉ ሲሆን ይህንን እንደ ሽፋን በመጠቀም ግን ‹‹ጥፋታችንን ስላመንን ህዝብ ይቅርታ ያደርግናል›› የሚል ማደናገሪያ ከማቅረብ ወደ ኋላ አላሉም፡፡
በተጨማሪም በአገዛዙ ስልጠና ላይ በሚሊሻና በአገዛዙ መከላከያ መካከል አለመግባባት እንዳለ አፍ አምልጧቸው የተናገሩት ደሰላኝ ጣሰው ልዩሃይል ማፍረሳቸው የጸጸታቸው በሚመስል ሁኔታ የአድማ ብተና ፖሊስ ሰራዊት እየገነባን ነው ብለዋል፡፡
አክለውም በጦርነቱ ሚሊሻውን እያስጨፈጨፉት እንደሆነም በራሳቸው አንደበት ሲያረጋግጡ ለአገዛዙ ሰራዊት ጥይት ማብረጃ ሆኖ እያገለገለ ያለውን ቅጥረኛ ሚሊሻ አራክሰው አቅርበዋል፡፡
ደሳለኝ ጣሰው ግማሽ ሰዓት በፈጀው መግለጫው በበርካታ ጉዳዮች በተለይም ፋኖን አዳክመናል በሚለው ፕሮፓጋንዳቸው እንደተለመደው ከእውነታው የራቁ ንግግሮችን አድርገዋል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion