የተጠናቀቀው የጎንደር እዝ ምስረታ

የጎንደር እዝ ምስረታ ተጠናቆ በአስተባባሪ አርበኞቹ በኩል ይፋ ተደረገ

ብልጽግና ተቆጣጥሬዋለሁ ፣ አዳክሜዋለሁ ሲለው የነበረው የጎንደር ትግል ይበልጥ ጎልቶ መውጣት ጀምሯል፡፡ አብይ አህመድ ታላቁን የጎንደር ትግል ፣ የአማራን የፋኖነት ምልክት በዝናሽ ታያቸውና በአገኘው ተሻገር የመንደር ፖለቲካ ሸብቤዋለሁ ብሎ ቢያስብም እንደ አብዮት ፈንድቶ ወጥቷል፡፡

የአማራን የአንድነት ጉዞ የሚያበስር ታላቅ ዜናም ከአጼዎቹ ምድር ተሰምቷል፡፡ የጎንደር ምድር የአንድነትን ቀዳሚ ዘማሪ ቴዎድሮስን ያፈራች ናትና የዛሬ ልጆቿም ወደ አንድነት በመምጣት አማራን አንድ ሊያደርጉ ተነስተዋል፡፡በዚህም በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የጎንደር እዝ ምስረታ በታላላቆቹ አርበኞች ይፋ ተደርጓል፡፡ቀዳሚ ፋኖዎቹና አስተባባሪዎቹ እነ ሻለቃ መሳፍንት ፣ እነ ሻለቃ ሰፈር መለስ ለአማራ ህዝብ ብሎም ለኢትዮጵያ ህዝብ የጎንድር እዝ ምስረታን መጠናቀቅ አሳውቀዋል፡፡በዚህም ካሁን በኋላ የጎንደር ፋኖዎች በአንድ እዝ በመዋቀራቸው ፣ የጎንደር እዝ ፋኖ በሚል እንደሚጠሩ የእዙ የበላይ ጠባቂ ምስረታውን አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

የአማራ ፋኖ የጎንደር እዝ የበላይ ጠባቂ ሆነው የተመረጡትም አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ሰብሳቢ ፣ አርበኛ አረጋ አለባቸው ምክትል ሰብሳቢ ፣ ሻምበል መሰረት አለሙ ጸሃፊ ፣ አርበኛ ደስታ ደመላሽ የሎጀስቲክ ሃላፊ ፣ አርበኛ ሰፈር መለስ የፋይናንስ ሃላፊ ፣ ሻምበል ገብሩ ልይህ የፋይናንስ ጸሃፊ አርበኛ እሸቴ ባይህ የፋይናንስ ቁጥጥር ሃላፊ በመሆን ተመርጠዋል፡፡ በዚህ የእዝ ምስረታም በጎንደር ከተማ ዙሪያ የሚንቀሳቀሰውን የቴዎድሮስ ብርጌድ ሲመራ የነበረው ሻለቃ ሃብቴ ወልዴ በአዛዥነት ተመርጧል፡፡ሻለቃ ውባንተ ምክትል አዛዥ ፣ ሻለቃ አንተነህ ድረስ የአስተዳደር ሃላፊ ፣ አርበኛ ደረጄ በላይ ዘመቻ መምሪያ ሃላፊ ፣ አርበኛ ሲሳይ አሸብር ምክትል ዘመቻ መምሪያ ሃላፊ ፣አርበኛ ባሻህ ስጦታው የፋይናንስ ሃላፊ ፣ ሻለቃ መለስ ተሾመ ፐርሶኔል ፣ ኮማንደር ሳሙኤል ሎጀስቲክ ሃላፊ ፣ ሻምበል አምሳሉ የፋይናንስ ጸሃፊ ፣ አርበኛ ብርሃኑ ነጋ የፋይናንስ ቁጥጥር ፣ ሻለቃ ባዬ ቀናው የፋይናንስ ኦዲተር ሆነው የተመረጡ አመራሮች ናቸው፡፡ይህንን እዝ የመሰረቱት የየፋኖ አደረጃጀቶችም አርበኞች ክፍለጦር ፣ ጎንደሬው በጋሻው ክፍለጦር ፣ በጌምድር ክፍለጦር ፣ ጭና ክፍለጦር ፣ ጉና ክፍለጦር ፣ ጎቤ ክፍለጦርና ድዋ ክፍለጦር ናቸው፡፡በአሁኑ ሰዓት እዝ እነዚህን ክፍለጦሮች ያካተተ ቢሆንም በሂደት ሌሎችንም እንደሚጨምር በመግለጫው አሳውቋል፡፡የእዙ የበላይ ጠባቂ ጎንደር እዝ ብለው ከመሰረቱት ውጪ ሌላ መመስረት እንደማይቻልም አስገንዝቧል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion