የላስታ ፋኖዎች መልዕክት

ላሊበላን በፈለግነው ሰዓት እንይዛለን ያሉት የላስታ ፋኖዎች የአገዛዙ ጦር ከአንድ ከተማ ውጪ የተቆጣጠረው ቦታ እንደሌለ ገለጹ
በወሎ እዝ ፋኖ የላስታ አሳምነው ክፍለጦር አባልትና አመራሮች  በላስታ ባሉ ከተሞች ከአንዱ በስተቀር የአገዛዙ ሃይል የለም ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ በከተሞቹም ሆነ በገጠር ቀበሌዎች ያለነው እኛ ነን ሲሉ ለአማራ ድምጽ ተናግረዋል፡፡
"ታሪካዊቷን ከተማ ላሊበላን በፈለግነው ሰዓት መቆጣጠር እንችላለን" ሲል የገጸው የክፍለጦሩ ምክትል አዛዥ ኮማንዶ ፍቅሩ ሙልዬ "በላስታ አውራጃ እስካሁን ድረስ የአገዛዙ ጦር ንጹሃንን ያጠቃል እንጂ ፋኖን አይገጥምም" ብሏል፡፡
"ጭዕፍጫፊውን የአገዛዙን ሃይል እኛ ነን እያጠቃነው ያለነው ሲል የሚገልጸው ፋኖ ፍቅሩ ሙልዬ  "መከላከያ ዳር ድንበር የመጠበቅ ሃላፊነቱን ትቶ መሃል ሃገር ላይ ህዝብ እያሰቃየ ነው" ይላል፡፡
ሆኖም በቅርቡ ይህንን ግፉን አስቁመን ከክልሉ አሳደን እናስወጣዋለን የሚለው አዛዡ የላሊበላ ልጆች ፣ የአሳምነው ግርፎች ከምንግዜውም በላይ መደራጀታቸውን አሳውቋል፡፡ ብልጽግና ፋኖንም ሆነ የአማራን ህዝብ ፈጽሞ አያሸንፍም ሲልም ገልጿል፡፡
መቶ አለቃ ተስፋዬ አበበ እርቅ ይሁን በበኩሉ ከአየር ሃይል ወደ ፋኖ መቀላቀሉን አሳውቆ ለሚሊሻና ለአድማ ብተና ፖሊሶች መልዕክት ሰዷል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion