የአገዛዙ ውድቀት በወሎ ግዛት


 በዋርካው ምሬ ወዳጆ የሚመራው የምስራቅ አማራ ፋኖ ድል ሲያደርግ መዋሉን አስታወቀ
በአማራ ፋኖ አንድነት ምክር ቤት የምስራቅ አማራ ፋኖ በጦር ግንባር የአገዛዙን ሃይል እያንኮታኮተው እንደሆነ ይፋ አድርጓል፡፡
ሳምንታትን የተሻገረው ጦርነት ለፋኖ ያልተጠበቀ ድል ሲያመጣ ውጊያውን አጥንቼ ገብቻለሁ ላለው ብልጽግና ደግሞ የውርደት ዶፍ እያዘነበ ይገኛል፡፡
‹‹ዛሬ ጥር 25 /2016 ከወትሮው በተለየ መልኩ ታላቅ ድል በራያ ግንባር ተሰርቷል። የፌደራል ዋናው ጥቁር አስፓልት በምስራቅ አማራ ፋኖ እጅ ከገባ ሰነባብቷል። ይህን መንገድ ለማስከፈት ጠላት ደጋግሞ ቢሞክርም የገጠመው እጣፈንታ ሽንፈትና ውርደት ሆኗል።›› ብሏል ፋኖ፡፡
የስፍራው ዘገባ ‹‹ዛሬ ጠላት የመጨረሻ ሀይሉን መንገድ ለማስከፈት ብሎ በሁለት አቅጣጫ ጦርነት ቢከፍትም የምስራቅ አማራ ፋኖ ክንድ እሚቀመስ ሆኖ አላገኘውም።›› ሲልም አክሏል፡፡
ከወልድያ አቅጣጫ የአገዛዙ ወታደርና ቅጠረኛው አድማ ብተና በኦራልና በፓትሮል ቢመጣም ጎብየን ሳያልፍ ካላኮርማ ብርጌድ አሚድ ወንዝ ላይ ሁሉም የጠላት ሃይል ከነ መኪኖቻቸዉ መደምሰሳቸውንም ገልጧል፡፡
ከወደ ትግራይ አቅጣጫ የመጣዉ የመጀመሪያዉ ሀይል መንገድ ተከፍቶለት ቆቦን አልፎ መጀሎ እንዲገባ ከተደረገ በኋላ መጀሎ እንደገባ ዞብል አምባ ብርጌድ ወጥመድ የገባዉን የብርሃኑ ጁላ ቅጥረኛ ወታደር ክፉኛ እንደመታው ዘገባው አክሏል፡፡
መንጀሎ ሰተት ብሎ የገባው የብልጽግና ሀይል ተጨማሪ ሀይል ከአላማጣ እንዲጨመርለት ቢጠይቅም ዋጃን እንዳያልፍ በሀውጃኖብርዴድ፥በረኸኛውብርጌድና ሞላ ደስዬ ብርጌድ በቆረጣ እየተፋለሙ መሆኑንም ለማወቅ ተችሏል፡፡
አገዛዙ በአሁኑ ሰአት ወደ ሰሜን፤ ወደ ደቡብም ሆነ ምዕራብም መውጣት ባለመቻሉ የምስራቁን ክፍል በመጠቀም ወደ አፋር ክልል ለመውጣት እንቅስቃሴ እያደረገ እንደሚገኝ ከስፍራው የወጣው መረጃ ያሳያል፡፡
ከመርሳ፣ ውጫሌ፣ ወርጌሳና ጊራና ምንም አይነት አገዛዙ እንቅስቃሴ እንዳይኖር መደረጉንና የምስራቅ አማራ ፋኖ ባለሽርጡና መብረቁ ብርጌድ በመናበብ አካባቢውን መቆጣጠራቸውን ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ከምስራቅ አማራ ፋኖ የተሰማው ሌላው ጉዳይ ከአፋር ተጋዮች ጋር አብሮ የመስራት ስምምትን የተመለከተ ነው፡፡
ምስራቅ አማራ ፋኖ ብልጽግና በቃኝ ብለው ጫካ ከገቡ የአፋር ታጋዮች ጋር ለወራት ከዘለቀ ንግግር በኋላ አብረው ለመስራት እና ብልጽግና መራሹን መንግስት በትግል ለመጣል ውህደትን መፈጸማቸው ተሰምቷል፡፡
የስምምነቱን ዝርዝር ጉዳዮች ለማጣራት ሮሃ ያደረገችው ጥረት በአካባቢው ካለው የግንኙነት መስመር ጋር በተገናኘ ለጊዜው አልተሳካም፡፡

0 Comments

Login to join the discussion