እነ ሽመልስ በአማራ ክልል
አማራን እየጨፈጨፉ ያሉት እነ ሽመልስ አብዲሳ "የአማራን ህዝብ ስለሰላም አወያዩ" በሚል የተሰራጨው ዜና እያነጋገረ ነው
አዳነችንና ደስታ ሊዳሞን በጎንደር ፣ ሽመልስንና አብርሃም በላይን በሰቆጣ ፣ አህመድ ሺዴንና ርስቱ ይርዳውን በደብረ ታቦር ፣ አለሙ ስሜን በገንደ ውሃ ፣ መስጠፌ መሃመድን በባህርዳር ያሰለፉት አብይ አህመድ ሁለት አላማ ለማሳካት ጥረዋል ፣ ምንም እንኳን ሁለቱም ባይሳካላቸውም፡፡
አንደኛው ከአለም አቀፉ ማህበረሰብ የሚመጣባቸውን ተጽዕኖ ለመቋቋም ክልሉ ሰላም ነው አመራሮቼንም ልኬ ህዝብ እያወያየሁ ነው ለማለት ያለመ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ እየተፈረካከሰ ያለውን መንግስታቸውን አቅምና አንድነት እንዳለው ለላኳቸው ባልስልጣናትም ሆነ ለህዝቡ ለማሳየት ነው፡፡በግል ውሳኔያቸው ብቻ አገሪቱን የሚመሩት እኒህ ሰው በርካታ አመራሮቻቸው እየከዷቸው ሲሆን ፣ አሁን ካሉትም ጋር አለመተማመን ውስጥ ገብተዋል፡፡በዚህም የአማራ ህዝብ ትግል ሲገፋ ሊያፈነግጡ ይችላሉ ያሏቸውን አመራሮችንም "አማራን እንኳን እያሸነፍኩ ነው" ለማለት አስበው ነው ይህን ጉዞ ያዘጋጁ፡፡ነገር ግን አብዛኛዎቹ ባልስልጣናት በመኪና የመንቀሳቀስ ስጋት ስለነበረባቸው በጦር ሄሊኮፕተሮች ጭምር መንቀሳቀሳቸውን የሰማን ሲሆን በገቡባቸው 15 ከተሞችም በከፍተኛ ወታደራዊ እጀባ ሲጠበቁ መቆየታቸው ታውቋል፡፡
እነዚህ አመራሮችም በከተማዎቹ ውለው እንዳላደሩና ከክልሉ በፍጥነት እንደወጡ ነው የተነገረው፡፡
የሆነው ሆኖ የአማራ ህዝብ ልቡም ፣ ሃሳቡም በትግል ላይ ካሉ ልጆቹ ጋር ሲሆን ፣ ያልሞት ባይ ተጋዳይ ውጊያ እያደረገ ያለው ብልጽግና ይህንን ህዝብ ከጎኔ አደርጋለሁ በሚል የማይወጣው ዳገት ፣ የማይወርደው አቀበት እንደሌለ እያሳየ ነው፡፡ለዚህም በአማራ ህዝብ ላይ የርሃብ አዋጅ ያወጁትን አቶ ሽመልስ አብዲሳን "የአማራን ህዝብ አውያዩ" የሚል የስላቅ ዜና እያስነገረ ነው፡፡
አማራውን በማንነቱ በየማጎሪያው የከተቱትን አዳነች አቤቤን የጎንደርን ህዝብ አወያዩ ሲልም በአማራ ላይ ለመቀለድ ሞክሯል፡፡
በጎንደር የተገኙትን አዳነችን ጨምሮ በተለያዩ ከተሞች "ህዝቡን አወያየን" በሉ የተባሉ የብልጽግና ሹማምንት በየአዳራሹ ተቃውሞና ከባድ ዝምታ እንደገጠማቸውም ተነግሯል፡፡በየመድረኩ የውሸት ጭብጨባ ሲያስተናግዱ የኖሩት አዳነች አቤቤም በጎንደር ይህ ስላልገጠማቸው እንደተበሳጩም ነው የተነገረው፡፡የሆነው ሆኖ አማራው ከትናንት እስከ ዛሬ እየጨፈጨፉት ያሉትን እነሽመልስ አብዲሳን ነፍጥ አንስቶ እየታገላቸው በመሆኑ በአዳራሽ የሚወያይበት ጊዜ የለውም፡፡ነገር ግን አገዛዙ በካድሬ በተሞሉ አዳራሾችና በግዳጅ በመጡ አባቶች የመሸቀል ስራውን ገፍቶበታል፡፡
Login to join the discussion