በጎጃም ግዛት የፋኖ እርምጃ


 በመርዓዊ ግምባር የአገዛዙን የጦር አዛዥ ጨምሮ በርካታ ሰራዊት ሙሉ በሙሉ መደምሰሱን የጣናው መብረቅ ብርጌድ አስታወቀ

የአማራ ህዝብ ወታደራዊ አቅም የሆነው የፋኖ ሰራዊት ከመርዓዊው የአገዛዙ ጭፍጨፋ በኋላ አራስ ነብር በመሆኑን በጎጃም ግዛት የእርምጃ አድማሱን በማስፋት በአገዛዙ ላይ የደመላሽ ሚናውን በመወጣት ላይ እንደሚገኝ ታውቋል፡፡
ሰሞኑን ደማቅ ታሪክ እየጻፈ የሚገኘው በባህርዳርና አካባቢው በስፋት የሚንቀሳቀሰው በአማራ ህዝባዊ ሃይል የጣናው መብረቅ ብርጌድ ዛሬም በርካታ ቁጥር ያለውን የብልጽግና ስልጣን ጠባቂ ሰራዊት ከእነጦር አዛዡ ከአፈር ደባልቆታል፡፡
የጣናው መብረቅ ብርጌድ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ ዳዊት ሽፈራው የጦር ግምባር ድሉን አስመልክቶ ለሮሃ ከስፍራው በሰጠው ማብራሪያ  አምስት በሚሆን ፓትሮል ተጭኖ የመሸንቲ አካባቢው ሲያውክ የነበረው ሃይል ከጥቂት የተኩስ ልውውጥ በኋላ ቆጥቆጥማ አካባቢ ሲደርስ ሙሉ በሙሉ መመታቱን አስረድቷል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጎጃም ምድር አሁንም የፋኖ ተጋድሎ ሲቀጥል በዛሬው ዕለትም በደጀን ወረዳ አባይ ሸለቆ እሰከ ምንጅ ቀበሌ ድረስ ፋኖ ከአገዛዙ ሰራዊት ጋር ትንቅንቅ ውስጥ እንደሚገኝና የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ከባድ መሳሪያ በመጠቀም ነፍሱን ለማትረፍ እየተንደፋደፈ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡
በጎጃም ሁሉም ነገር ከአቅሙ በላይ የሆነበት አገዛዙም በጦር ሜዳ የሚደርስበትን ምት መቋቋም ሲያቅተው ያልታጠቁ ወገኖችን እያሰቃየ ይገኛል፡፡
ላለፉት ሶስትና አራት ቀናትም በባህር ዳር ከተማ የፍተሻ ስልጠና በወሰዱ ሚሊሽያዎችና ፖሊሶች የቤት ለቤት ፍተሻ እየተደረገ እንዳለ የነገሩን የከተማዋ ነዋሪዎች ፋኖን ትደግፋላችሁ በሚል ማዋከብና በፍተሻ ሰበብ ንብረት ዝርፊያው እንዳማረራቸው ለሮሃ ገልጸዋል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion