የአርበኛ ዘመነ ካሴ ምላሽ


"ወንድሞቻችን ተረድተውትም ይሁን ሳይረዱት የጠላቶቻችን ፈረስ ሆነው ሲያገለግሉ ማየት አንፈቅድም" ሲል አርበኛ ዘመነ ተናገረ
አርበኛ ዘመኔ ካሴ አደረጃጀትን አስመልክቶ በሰጠው ማብራሪያ ፣ "የጎጃም እዝ ወታደራዊ አላማን ይዞ የተቋቋመ ነው" ያለ ሲሆን ፣ " 'እዙ በእናንተ መጥፋት የተፈጠረ ነው' የሚሉት ግን የእኛን ትግል የማያውቁ ናቸው" ብሏል፡፡ "የእዙ አመራሮች ወንድሞቻችን ናቸውና እንደወንድምም እየተነጋገርን" ነው ሲል ገልጿል፡፡
"ሆኖም ግን ወንድሞቻችን ተረድተውትም ይሁን ሳይረዱት የጠላቶቻችን ፈረስ ሆነው ሲያገለግሉ ማየትን አንፈቅድም" ብሏል፡፡
አርበኛው ያለውን እውነት ይፋ ባደረገበት በዚህ ማብራሪያው በእስር ቤት ከቆየባቸው ዘጠኛ ወራት በባህርዳር እስከስነበተባቸው 2 ወራት ድረስ ሲያደርገው ስለነበረው የትግል እንቅስቃሴ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡
"ይሁን እንጂ "ዘመነ ጠፍቷል" የሚሉ የዋሆች አስረስ በጫካ ሆኖ እኔ ደግሞ በባህርዳር ከአገዛዙ ባልስልጣናት ቢሮ ጀርባ ሆኜ ሳደርገው ከነበረው ትግል እስካሁን ስላለው ነገር ያልተረዱ ናቸው" ብሏል፡፡
ዘመነ ከብልጽግና ጋር ተደራድሯል እያሉ የሚያወሩ ጠላቶችም ነበሩ ሲል ተናግሯል፡፡
አርበኛው አክሎም "የጠላቶቻችን ልጓም ጎታች ሆነን ጠላቶቻችንን አራት ኪሎ አናስገባም ፣ ይህ ፈጽሞ አይቻልም" ሲል ገልጿል፡፡ ይህ ትግል የጎጃምን ፣ የሸዋን ፣ የጎንደርን ፣ የወሎን ትከሻ ይፈልጋል ሲልም አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion