የአማራ ክልል ውሎ

በላሊበላ አቅራቢያ ከባድ ውጊያ ሲካሄድ በባህርዳር ደግሞ በፋኖ ጥቃት ተፈጽሟል
በላስታ ቀጠና ሲካሄድ የነበረው ውጊያ ቀጥሎ ፣ ዛሬ አዳሩን ሹምሽ ውሃ  አየር ማረፊያ ዙሪያ በፋኖና በአገዛዙ ሰራዊት መካከል ከባድ ትንቅንቅ ተካሂዷል፡፡
በወሎ እዝ የላስታ አሳምነው ክፍለጦር ስር ካሉ አስራ አምስት ሻለቃዎች መካከል አንዷ የሆነችው በብርጋዴር ተፈራ ማሞ የተሰየመችው ሻለቃ በአየር ማረፊያው ዙሪያ በአገዛዙ ወታደሮች ላይ ጥቃት ከፍታ በርካታ ወታደሮችን ሙትና ቁስለኛ አድርጋለች፡፡
በዚህ በሹምሽ ውሃ አየር ማረፊያ ዙሪያ የዐቢይን ሰራዊት ቀለበት ውስጥ አስገብተው ሲለበልቡት ያደሩት የአሳምነው ጽጌ ልጆች በርካታ ወታደሮችን ሲገድሉ አምስት መኪና ሙሉ ወታደሮችን ቁስለኛ አድርገዋል፡፡
ትናንት ሌሊት የጀመረው ውጊያ በትናንትናው እለት ቀጥሎ ከላሊበላ በቅርብ ርቀት ከሰኞ ገበያ እስከ ሰሜኑ ባለው ፣ በደጋማው በኩል ደግሞ እስከ ደጎዛይ ፣ በአይናማ በኩል ደግሞ በቅዱስ አርቤ ዙሪያ ፣ እንዲሁም በሹምሽ ውሃ ኤርፖርት በኩል  ከባድ ውጊያ  መካሄዱ ታውቋል፡፡
ዛሬ ሌሊቱን ውጊያው በሹምሽ ውሃ የቀጠለ ሲሆን ንጋት ላይ የአገዛዙ ወታደሮች ሙትና ቁስለኛ ሆነው ጦርነቱ ቆሟል፡፡ የአገዛዙ ጦርም ሙትና ቁስለኛቸውን እየሰበሰቡ መሆኑን የላስታ አሳምነው ጽጌ ክፍለጦር ዘመቻ መምሪያ ሃላፊ ፋኖ ታዘበው ሻምበል ተናግሯል፡፡
በሌላ በኩል የአማራ ፋኖ የጎጃም እዝ አባላቶች በባህርዳር ከተማ በፈፀሙት የቦምብ ጥቃት ፋኖን ለማጥቃት ሊንቀሳቀሱ የነበሩ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ የፖሊስ አባላቶች ሲገደሉ መርማሪ ፖሊሷን ጨምሮ ሌሎች የፖሊስ አባላት ደግሞ ቆስለዋል።
ይህ በእንዲህ እንዳለም በዛሬው እለት በሰከላ ግሽ አባይ ከተማ ገበያ ላይ ቦምብ ተጥሎ በርካታ ንጹሃን መገደላቸው ተሰምቷ፡፡ በጥቃቱ ምን ያህል ሰዎች ላይ ጉዳት እንደደረሰ ግን ለጊዜው አልታወቀም፡፡

0 Comments

Login to join the discussion