ነጻ እየወጡ ያሉ የአማራ መሬቶች
በአራቱም የአማራ ግዛቶች በቀጠለው ውጊያ በርካታ ስፍራዎች በፋኖ ስር እየገቡ ነው
በአማራ ክልል በሰሜን ወሎ ፣ በጎንደርና በጎጃም እየተካሄዱ ያሉ ውጊያዎች የቀጠሉ ሲሆን በሸዋ ያልተጠበቁ ጀብዱዎች ተፈጽመዋል፡፡ በዚህም በሰሜን ወሎ መቄት ፣ ገረገራና ራያ አካባቢዎች ከባድ ትንቅንቅ እየተካሄደ ነው፡፡
ላለፉት ቀናት በዚህ ቀጠና ከአንድ ክፍለጦር በላይ የዐቢይ አህመድ ወታደር ተሰማርቶ የነበረ ቢሆንም ከዚህ ውስጥ ከሶስት ሻለቃ በላይ የሚሆነው ብትንትኑ ወጥቷል፡፡
በዚህም ከከባድ መሳሪያ ጀምሮ እስከ ቀላል መሳሪያ ድረስ በፋኖ የተማረከ ሲሆን በዚህ ውጊያም ፋኖ ራሱን በትጥቅ አጠናክሯል፡፡
በዚሁ በሰሜን ወሎ መቄት ደብረ ዘቢጥ በሚባል አካባቢ የነበረው የብልጽግና ሃይል በርሃብና በጥማት እንዲመናመን ያደረገው ፋኖ የእቴጌ ጣይቱን የአድዋ ጦርነት ስትራቴጂ ተጠቅሞ ውጤት አስገኝቷል፡፡
በአካባቢው የነበረው የአገዛዙ ወታደርም ሆዱ ሲጎድልበት አካባቢውን እየለቀቀ ተበትኗል፤ የተረፈውም በየመንገዱ ተለቅሟል፡፡ በስፍራው የቀረውም ትንሽ ሃይል መሆኑ ታውቋል፡፡
ከእነዚህም ውስጥ በርካቶች እየተማረኩ ሲሆን በዛሬው እለትም ከደብረዘቢጥ የተነሱ 50 የአገዛዙ ወታደሮች ወደ ጋይንት ተሻግረው እጃቸውን ለፋኖ ሰጥተዋል፡፡
የራስ ጋይንት ፋኖዎችም እጃቸውን በሰላም የሰጡ ወታደሮችን ተቀብለዋል፡፡
በዚህ ቀጠናም የወሎና የጎንደር ፋኖዎች በትብብር እየሰሩና ተናበው የአገዛዙን ጦር ገዝግዘው እየጣሉ ስለመሆናቸው ተነግሯል፡፡
ሰሞኑን በተደረጉ እልህ አስጨራሽ ውጊያዎችም ጀግኖቹ የገብርዬ ልጆች ከንፋስ መውጫና ከስማዳ ወገዳ ከተሞች ውጪ የጋይንትና የእስቴ ወረዳዎችን ሙሉ በሙሉ ሊባል በሚችል ደረጃ መቆጣጠሩ ታውቋል፡፡
ወሳኝ የሚባሉ ድሎችን በአካባቢው እያስመዘገበ ያለው የጉና ክፍለጦር አርሶ አደሩን ጭምር አስተባብሮ የራሱን መሬት ነጻ አውጥቷል፡፡ ወታደራዊ ጠቀሜታ ያላቸውን ስፍራዎችን ጭምር በቁጥጥሩ ስር ማድረጉ ታውቋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በጎጃም አዴትና ዴንሳ ባታ ከፍተኛ ውጊያ ሲካሄድ የሰነበተ ሲሆን ፣አዴት ከተማም በፋኖ እጅ ገብታለች፡፡ በዴንሳ ባታ ሰፍሮ የሚገኘውን የአገዛዙን ወታደር ለመምታትም ከፍተኛ ህዝባዊ እንቅስቃሴ እየተደረገ ሲሆን የአማራ ፋኖ በጎጃምም ከባድ ማጥቃት እያደረገ ነው፡፡ ይህ ከባድ ጥቃት እስከ ብራቃት የዘለው ውጊያ ተከፍቷል፡፡
ከቲሊሊ እስከ ሰከላ ለሶስተኛ ቀን የቀጠለ ትንቅንቅ እየትካሄደ ሲሆን ፣ የብልጽግና ጦር ያልጠበቀ እሳት እየወረደበት ነው፡፡
በጎጃም ላለፉት አራት ቀናት እየተካሄዱ ያሉ ውጊያዎች የብልጽግናን መንደር ብርክ ብርክ ያሰኙ ፣ ውሃ ውሃ ያስባሉ ናቸው፡፡በዚሁ በጎጃም አገው ምድር ከአዲስ ቅዳም እስከ ፋግታ ዛሬ ረፋዱን የጀመረው ውጊያ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
የአማራ ፋኖ በጎጃም የጀመረው ማጥቃትም አራተኛ ቀኑን የያዘ ሲሆን ፣ መንገዶችም በፋኖ ትዕዛዝ መሰረት ሙሉ በሙሉ እየተዘጉ ነው፡፡
በዚሁ በጎጃም ቋሪትም የአገዛዙ ሃይል ሙትና ቁስለኛውን እንኳን መሰብሰብ እያቃተው ሲሸሽ ታይቷል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በሸዋ የገባው የአገዛዙ ሰላይና ተዋጊ ቡድን በሸዋ ፋኖዎች እየተለቀመ ስለመሆኑ ታውቋል፡፡
እንዲሁም በሸዋሮቢት ከተማ ሆድ አደሮቹ የከተማዋ ፖሊስ አዛዥ ኢንጂነር ዘርዓይና የከተማው ሰላምና ደህንነት ሃላፊ አቶ ፍጹም በአማራ ፋኖ በሸዋ እዝ በተሰራ ኦፕሬሽን ተገድለዋል፡፡
Login to join the discussion