የታጋይ ገበሬዎች ጥሪ

"የአማራ ገበሬን ጨምሮ የክልሉ ህዝብ በአንድ ላይ ሊነሳ ይገባል" ሲሉ በጦር ግምባር ያሉ የጎንደር ገበሬዎች ገለጹ
አማራ እያካሄደው ያለው የህልውና ተጋድሎ ሴትና ወንዱ ፣ አርሶ አደርና ነጋዴው ፣ መምህሩና ደቀ መዝሙሩ ዳር እስከ ዳር በጋራ የቆሙበትና የተሳተፉበት ነው፡፡
ከጉና ተራሮች እስከ ሸዋ ኮረብታዎች ፣ ከጣና ሃይቅ እስከ ከሰም በረሃዎች ፣ ከራያ ምድር እስክ እስከ አገው ምድር የተቀጣጠለ ታላቅ ተጋድሎ ነው፡፡
ማዳበሪያ የተነፈገው  ፣ መኖር የተከለከለው የአማራ ገበሬ እርፍ የጨበጠ እጁ የጥይት ምላጭ መሳብ ጀምሯል፡፡
በደቡብ ጎንደር የሚገኙ አርሶ አደሮችም የህልውና ትግሉን ተቀላቅለው የአገዘዛን ጦር ከፋኖ ልጆቻቸው ጋር አብረው እያበራዩት ይገኛሉ፡፡
እነዚህ ገበሬዎች ግፍ አንገሸገሸን ፣ ቤታችን ቁጭ ብሎ መገደል ሰለቸን ብለው የብልጽግናን ጦር ገጥመዋል፡፡ ሌላውም የአማራ ህዝብ ይህንኑ እንዲያደርግ ጠይቀዋል፡፡
ገበሬዎቹ ሁሉም የአማራ ህዝብ መሳሪያ ያለው መሳሪያውን ፣ ገጀራም ያለው ገጀራውን ይዞ አገዛዙን ከክልሉ ሊያሰወጣው ይገባል ሲሉም ተደምጠዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በወሎ እዝ የመቅደላ ጽናት ክፍለጦር አመራሮች በውጫሌ ስለተደረገው ውጊያና ከተማዋን ስለያዙበት መንገድ ለአማራ ድምጽ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
የክፍለጦር የሰው ሃይል አመራር ፋኖ ፍቃዱ አሰፋ በኮንክሪት የተሞሉ አራት ምሽጎችን ሰብረን ነው ከተማዋን የተቆጣጠርነው ብሏል፡፡ በዚህም ከልጅ እያሱ ክፍለጦር ጋር ተናበን ሰርተናል ሲል ገልጿል፡፡


0 Comments

Login to join the discussion