የወሎና የሸዋው ትንቅንቅ

በወሎና በሸዋ ግዛቶች ከባድ ትንቅንቅ የታየበት ውጊያ ሲካሄድ ደሴም በከበባ ውስጥ ገብታለች
በደቡብ ወሎ አምባሰልና ተሁለደሬ ወረዳዎች ከሶስት ቀናት ጀምሮ እስከ ዛሬ የዘለቀ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑ ታውቋል፡፡
በአካባቢዎች እየተካሄደ ያለው ውጊያ ቀጥሎ ትናንት ውሎውን ከባዱ ተጋድሎ ደሴ ዙሪያ ላይ ደርሷል፡፡
በደቡብ ወሎዋ መቀመጫ ደሴ ዙሪያ 20 ኪሎሜትር ድረስ ባሉ ገጠራማ አካባቢዎች እየተካሄደ ባለው ውጊያ የአገዛዙ ወታደር ከፍተኛ ኪሳራ እያስተናገደ ነው፡፡
በተጨማሪም ሮቢት ፣ ጎልቦ ፣ ይስማ ንጉስና ጭሳ በተባሉ አካባቢዎች እየተካሄደ ባለው ውጊያ በፋኖ ከተማረከ የብልጽግና ጦር አመራር የተገኘው የድምጽ ቅጂም ለፋኖ እጅግ ጠቀሜታ ያለው ሆኖ ተገኝቷል፡፡
ይህ የድምጽ ቅጂም "የተሁለደሬ ወረዳ የሚሊሻ ጽ/ቤት ሃላፊ ከሶስት ሳምንት በፊት መገደሉን ተከትሎ አሁን ያሉት ሚሊሻዎች አቅም የላቸውም ድጋፍ ጨምሩልን" የሚል ነው፡፡
በዚህ ውጊያም ሁለት አይሱዙ መሳሪያና ሬሽን በፋኖ ተማርኳል፡፡ እንዲሁም ብሬንን ጨምሮ ቀላል የማይባሉ መሳሪያዎች ተማርከዋል፡፡
በአጠቃላይ በደቡብ ወሎ እየተካሄደ ያለው ውጊያ በኩታበር ዙሪያ ባሉ ገጠራማ አካባቢዎችም ተባብሶ የቀጠለ ሲሆን ፣ ፋኖም ደሴ ለመግባት አፋፍ ላይ ደርሷል፡፡
በአምባሰልና በተሁለደሬ አካባቢዎች እየተካሄደ ያለው ውጊያ ያሰጋው የብልጽግና ሃይል ፣ ከባባድ መሳሪያዎችን ወደ ደሴ እያሸሸ መሆኑም ተሰምቷል፡፡
በተመሳሳይ በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ባለው ውጊያ ከመሃል ሜዳ ወደ አጣዬ እየተጓዘ የነበረን የብልጽግና ሃይል ቢጋ በተባለ ቦታ ላይ የፋኖ ሃይሎች ከበው ድባቅ መምታታቸው ነው የተነገረው፡፡
በዚህም ከባድ መሳሪያዎችን ጨምሮ ፋኖ በርካታ ተተኳሾን አግኝቷል፡፡
እንዲሁም በአጣዬ ዙሪያ አላላ ላይ እየተካሄደ ባለው ውጊያ ፋኖ በብልጽግና ጦር ላይ ከባድ ኪሳራ አድርሷል፡፡ ትናንት ማርፈጃውን የተካሄደው ይህ ውጊያ ለቀናት ጋብ እያለ የቀጠለ ነው፡፡
በተጨማሪም ከካራ ቆሬ እስከ ጨፋ ፣ ከመንዝ እስከ ጣርማ በር  እንዲሁም ከአጣዬ እስከ ካራ ቆሬ ባሉ አካባቢዎች ፋኖ ከባድ ትንቅንቅ እያካሄደ ይገኛል፡፡
የብልጽግና ሰራዊትም በፋኖ በሚደርስበት ከባድ ምት ውሃውሃ እያለ ነው፡፡
እንዲሁም በዚሁ በሸዋ ቀጠና በኦሮሞ ብሄረሰብ ዞን ከሚገኙ አካባቢዎች የተነሱ የኦነግ ታጣቂዎች ከአገዛዙ ሰራዊት ጋር በመጣመር ከማጀቴ ፣ መስኖ ውሃና ጨፋ ተብሎ የሚጠራ አካባቢ ድረስ ጥቃት በመክፈት ከ20 በላይ አርሶ አድሮችን ገድለዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የዐቢይ አህመድ ስልጣን አስጠባቂ የሆነው ጦር በፌስ ቡክ ገጹ ላይ ባሰፈረው ጹሁፍ " በቋሪት ፣ በአዴት ፣ በዱር ቤቴ ፣ በመርዓዊና በሊበን ከህዝብ ጋር ባደረግኳቸው ውይይቶች ፣ህዝቡ እንኳን መከላከያው መጣልን እያለ ነው" ሲል ለጆሮ የሚሰቀጥጥ ነጭ ውሸት አሰራጭቷል፡፡
የጎጃም ህዝብና ገበሬ ከሊቅ እስከ ደቂቂ ከፋኖ ልጆቹ ጋር ሆኖ የገደለውን ፣ ያሰቃየውን ፣ ጫካ ያስገባውን ፣ በየመንገዱ የረሸነውን ፣ በድሮንና በከባድ መሳሪያ የጨፈጨፈውን ፣ ማዳበሪያ የከለከለውን ፣ ወደ አዲስ አበባ እንዳይገባ ያገደውን አገዛዝና ይህን አገዛዝ የሚያገለግለውን ጦር እየታገለ ነው፡፡
የአገዛዙ ቅጥፈት ይቀጥልና "በውይይቱ የተሳተፉ የቋሪት ፣ አዴት ፣ መርሃዊ ፣ ዱርቤቴ እና ሊበን ነዋሪዎች ስለ ሰራዊቱ ሲነገረን የነበረው እና አሁን በተግባር ያገኘነው ፍፁም ተቃራኒ ነው ፤ ሀይማኖት ያስቀይራል ፣ሴት ልጅ ይደፍራል፣ የእምነት ተቋማትን ያወድማል ወዘተ በሚል ህዝቡን ቀስቅሰውታል ይህ ደግሞ ሀሰት ነው ብለዋል" ይላል፡፡
እውነት ነው ይህ ሃሰት ነው ፣ የዚህ ሰራዊት ግፍ በእነዚህ ሰዋዊ ቋንቋዎች ብቻ አይገለጽም የሚል አስተያየትም አሰጥቷል፡፡
ሰራዊቱ አይኑን በጨው አጥቦ ከሳምንታት በፊት በመርዓዊ ከተማ ነብሰጡር እናትና ነብሰ ያለወቀ ህጻንን ጨምሮ የ72 ዓመት አዛውንትን ከ115 ሌሎች ንጹሃና ጋር መጨፍጨፉን ዘንግቶ ዛሬ የመርዓዊና የጎጃም ህዝብ እንኳን መጣችሁልን እያለን ነው ሲል በህዝብ ተሳልቋል፡፡
በየግምገማዎቹ ፋኖን ማሸነፍ ያቃተን ህዝቡ ከጎኑ ስላለ ነው የሚለው ብልጽግና በየስብሰባዎቹ ደግሞ ህዝቡ ከጎኔ ሆኗል የሚል ጽሁፍ ያሰራጫል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion