የፋኖ ጉዞ ወደ አራት ኪሎ

ፋኖ አሰግድ መኮንን በሁለት ወር ውስጥ አራት ኪሎን እንገባለን ሲል ተናገረ
የሸዋ ፋኖ አዛዥ ከሆኑት ውስጥ አንዱ የሆኑት ኮማንደር አሰግድ መኮንን በሚቀጥሉት ሁለት ወራት ውስጥ አራት ኪሎን እንቆጣጠራለን ማለታቸውን ኢኤም ኤስ የተሰኘው ሚዲያ ዘግቧል፡፡
ፋኖ አሰግድ "መከላከያው ፈርሷል ፣ እየተዋጋን ያለው ሆድ አደር የአማራ ሚሊሻና አድማ ብተና ነው" እንዳሉም ነው የተዘገበው፡፡
በተመሳሳይ ከሸዋ መሃል ሜዳና ከደቡብ ወሎ ወረኢሉ በመነሳት በጌሼ ራቤ ፈረስ ቤት ተብሎ ወደ ሚጠራ አካባቢ የገባው የአገዛዙ ጦር በትምህርት ቤት ላይ ፈንጅ ማጥመዱ ነው የተነገረው፡፡
"ይህ ሃይል በፋኖዎች መከበቡን ሲያረጋግጥ ነው ይህንን ፈንጂ በትምህርት ቤት ውስጥ ቀብሮ የሸሸው"ተብሏል፡፡
ነገር ግን ከአካባቢው የአገዛዙን ጦር ያስወጡት ፋኖዎች የተቀበረውን ፈንጅ በባለሞያ ለማስወጣት እየሰሩ ነው፡፡
በተጨማሪም አካባቢውን ለቆ ሲሸሽ የነበረው የብልጽግና ጦር ከባድ መሳሪያዎችን በመተኮስ ከተማዋን እያነደደ መሆኑ ነው የተነገረው፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በጎጃም ቋሪት ወረዳ ገበዘ ማሪያም ከተማ ሰፍሮ የነበረው የብርሃኑ ጁላ ጦር በፋኖ ጠንካራ ክንድ ተመትቶ በመውጣቱ የአካባቢው ነዋሪዎች ደስታ እንደተሰማቸው ተናግረዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በደቡብ ጎንደር ጉና ክፍለጦር የእስቴ ደንሳ ብርጌድ የጣና ገላውዲዎስ ሻለቃን የተቀላቀለው የአገዛዙ ወታደር የዘመቻ መምሪያ ሃላፊ ፋኖን በፈቃዱ መቀላቀሉን ተናግሮ እየተደረገለት ባለው እንክብካቤም ደስተኛ መሆኑን ገልጿል፡፡
"እኔ የጎጃም ልጅ ነኝ ፣ እና መከላከያ እናቴ ቤት ገብቶ ጨውና በርበሬ ሲዘርፍ እያየሁ ከአገዛዙ ጦር ጋር አብሬ አልቆምም" ይላል ይህ የአገዛዙ የቀድሞ ወታደር ለአማራ ድምጽ በሰጠው አስተያየት፡፡

0 Comments

Login to join the discussion