የደብረብርሃኑ ውጊያና የባንኮች ዝርፊያ

በደብረብርሃን ዙሪያ ከባድ ውጊያ እንደተካሄደና የአገዛዙም ጦር የባንክ ዝርፊያ ላይ መሰማራቱ ተነገረ
በደብረብርሃን ዙሪያ ጎሸ ባዶ የገባው የአገዛዙ ሃይል በህዝቡ ላይ በከባድ መሳሪያ የተጋዘ ተኩስ ቢከፍትም ፣ ፋኖ ባደረገው ከባድ ተጋድሎ ጦሩ ሙትና ቁስለኛ ሆኖ ከስፍራው ወጥቷል፡፡
በትናንትናው እለት በዚህች በደብረብርሃን ዙሪያ ባለችው ከተማ የገባው ሃይል በህዝቡ ላይ ጭፍጨፋ ሲጀምር በዙሪያው የነበሩት ፋኖዎች እግር በእግር ተከትለው ገብተው አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው አስወጥተውታል፡፡
ተኩሱን ፈርተው ቤታቸውን ዘግተው የተቀመጡ ንጽኋን ጭምር ቤታቸው በላያቸው ላይ በከባድ መሳሪያ መውደሙ ታውቋል፡፡
ነገር ግን በፋኖዎች ከባድ ተጋድሎ ይህ ጨፍጫፊ ሃይል ኪሳራ አስተናግዶ አካባቢውን ለቆ ወጥቷል፡፡ በዚህም ወደ ተነሳበት ደብረብርሃን ከተማ ሸሽቷል፡፡
በዚህ ውጊያ ከ30 የሚበልጡ የአገዛዙ ጦር አባላት ከእነ መሳሪያቸው እጃቸውን ለፋኖ የሰጡ ሲሆን ከፊሎች ከውጊያው በፊት ጭምር ለፋኖ መረጃ ሲያቀብሉ የነበሩ ናቸው፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአገዛዙ ጦር በፋኖ እየደረሰበት ባለው ከባድ ሽንፈት ንጹሃንን እየጨፈጨፈና ቤታቸውን እያቃጠለ ነው ሲል የአማራ ፋኖ በጎጃም ቃል አቀባይ ፋኖ ማርሸት ጸሃው ተናግሯል፡፡
በዚህም ከሰሞኑ በአዴት የንጹሃንን ቤት ሲያቃጥል እንደነበረና በዛሬው እለት ደግሞ በሰከላ ከተማ ሶሶት ባንኮችን ማለትም ቡና ባንክ ፣ ንግድ ባንክና ዳሽን ባንክን የብርሃኑ ጁላ ጦር መዝረፉን ተናግሯል፡፡
ከዚህ ቀደምም በቲሊሊ 5 ባንኮችን ዘርፎ ወስዷል ሲል አስረድቷል ፋኖ ማርሸት፡፡

0 Comments

Login to join the discussion