የቀጠለው ውጊያ

በባህርዳር ዙሪያ ባሉ የጣና ሃይቅ አካባቢዎች ላይ ከባድ ውጊያ እየተካሄደ መሆኑ ተሰማ

የአገዛዙ ሃይል "በአንድ ሳምንት የምጨርሰው ኦፕሬሽን አለብኝ" በሚል አማራ ክልል ከገባ ስምንት ወራትን ቢያስቆጥርም አሁንም በአማራ ፋኖ ብርቱ ክንድ ያለው አቅም ሁሉ እየከዳው አይደለም የአማራ ክልል ኢትዮጵያም ከእጁ እየወጣች ነው፡፡
ፋኖ በአራቱም የአማራ ግዛቶች አማራን ለመጨፍጨፍና አንገት ለማስደፋት የገባውን ሃይል ማርኮና ደምስሶ እየጨረሰው መሆኑን በየግንባሩ ያሉ ሁነቶች ይመሰክራሉ፡፡
ጎጃምና ጎንደርና ከሚያጣምረው የታላቁ የጣና ሃይቅ ላይ ያለውን ዘጌ አካባቢን ለመቆጣጠር አገዛዙ ከባድ ውጊያ ከፍቷል፡፡
በወገርሳ ፣ በይማ ላላ እና በሊበን አካባቢ ያሉ ፋኖዎች እንፍራንዝ በተባለ አካባቢ ላይ የፋኖ ሃይሎች ሲግተለተል የመጣውን የብልጽግና ጦር ተመትቶ ተመልሷል፡፡
በዚህ በዘጌ ከተማ በሚገኝ ትልቅ ተራራ ላይ የሚገኘው የአማራ ራዲዮ አንቴና መመታቱም ነው የታወቀው፡፡
ምናልባትም በዛሬው እለት የሬዲዮ ስርጭት ላይሞር ይችላል የሚል ምረጃ ወጥቷል፡፡
ለሶሶት ቀናት የክልሉ የወረዳና የከተማ አስተዳደሮች በባህርዳር ስብሰባ ማካሄድ መጀመራቸውን ተከትሎ ከተማዋ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ወታደር እንደከበባትም ለማወቅ ተችሏል፡፡
በከተማዋ ያለው የጸጥታ ሃይል መሳሪያ ደቅኖ እየተንቀሳቀሰ ሲሆን ምን ያህል ስጋትና ፍራቻ እንዳደረባቸው ማሳያ ነውም ተብሏል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በትናንትናው እለት የሸዋ ፋኖዎች በሸዋ ሮቢት ከተማ የሚገኘውን የሬዲዮ ጣቢያ መቆጣጠራቸው ታውቋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በምስራቅ ጎጃም ደብረማርቆስ ከተማ የሚገኙ ነጋዴዎች በብልጽግና አሽከሮች ያልሰራንበትን ግብር ክፍሉ በሚል እየተገደድን ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡
ዐቢይ አህመድ በአማራ ላይ ያወጁትን ጦርነት ተከትሎ አማራ ህልውናውን ለማስጠበቅ በገባበት በዚህ ውጊያ ብልጽግና ከተሞችን በወታደርና በከባድ መሳሪያ ከቦ ህዝቡን እያስጨነቀ ሲሆን አሁን ደግሞ ግብር ክፈሉ እያለ ይገኛል፡፡
የፋኖ አመራሮች ደግሞ ሁሉም አማራ የግፍ ጽዋው እቤቱ ተቀምጦም ቢሆን ይደርሰዋል እና ወጥቶ ይታገል የሚል ተደጋጋሚ ጥሪ እያቀረቡ ነው፡፡
በተመሳሳይ በሰሜን ሸዋ የብልጽግና አሽከር የሆኑት የሚሊሻና የአድማ ብተና አባላት በሲያ ደብር ፣ ዋዩ እና ደነባ ህዝቡን ግብር ክፈሉ እያሉ እያስገደዱ ነው፡፡
የዐቢይ አህመድ መንግስት በአማራ ክልል ህዝቡን በጦርነት እያመሰ ለዚሁ ጦርነት ማስኬጃ የሚሆን ግብር ደግሞ ከህዝቡ መጠበቁ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡ ነገር ግን ህዝቡ ግብር አንከፍልም እያለና አድማ እየመታ መሆኑ ታውቋል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion