የጎጃም ግዛት ብርቱ ውጊያ

በዳንግላ ከተማ ዙሪያ ሶስት ቀናትን ባስቆጠረው ከባድ ውጊያ የአገዛዙ ጦር ከፍተኛ ኪሳራ ደረሰበት
በጎጃም ግዛት በፋኖ ቁጥጥር ስር የሚገኙ በርካታ አካባቢዎችን መልሶ ለመያዝ አለኝ የሚለውን ጦር ያሰለፈው የብልፅግና አገዛዝ ሃይል በፋኖ ኦፕሬሽን ተበታትኖ ሽንፈቱን ለመቀበል መገደዱን ለማወቅ ተችሏል።
የአማራ ፋኖ በጎጃም የራስ ቢትወደድ መንገሻ ጀምበሬ ብርጌድ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በዳንግላ ዙሪያ ባካሄዳቸው ልዩ ኦፕሬሽኖች በአገዛዙ ጦር ላይ ጠንካራ እርምጃ መውሰዱን ከግንባር የወጡ መረጃዎች ያመለክታሉ።
በትናንቱ ኦፕሬሽን በርካታ ቁጥር ያላቸው የአድማ ብተና ቅጥረኛ ወታደሮችና የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት አባላት ሙትና ቁስለኛ ሆነው መበታተናቸውም ተሰምቷል።
በአሁኑ ሰዓትም ጃዊ፣ ዳንግላ፣ ቲሊሊ፣ ኩቲት፣ ኮሶበር ዙሪያና አዋሳኝ የዞኑ አካባቢዎች አሁንም በፋኖ ቁጥጥር ስር እንደሚገኙም የአማራ ፋኖ በጎጃም አረጋግጧል።
የአማራ ፋኖ በጎጃም የቀጠናዊ ትስስር መምሪያ ሃላፊና የአዊ ዞን ፋኖ ሰብሳቢ ፋኖ የቆየ ሞላ በአካባቢው ላለፉት ቀናት መካሄዱ የቀጠለውን ውጊያ አስመልክቶ በተለይም ለአማራ ድምፅ በስልክ በሰጠው ማብራሪያ ድሉ የፋኖ ሆኖ መቀጠሉን አስረድቷል።
ፋኖ የቆየ ሞላ የአገዛዙ ጦር ላለፉት አስር ቀናት አልሞ የከሸፈበትን ጥቃት አስመልክቶም ተከታዩን ብሏል።


0 Comments

Login to join the discussion