ፓርላማው ስለ አቶ ክርስቲያን

ፓርላማው የግፍ እስረኛውን የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ ነው
የዐብይን ወሬ አድምጦ ከማጨብጨብ የዘለለ ሃላፊነት የሌለው ፓርላማ ነገ ሐሙስ መጋቢት 5/2016 ዓ.ም. በሚያካሂደው መደበኛ ስብሰባ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ተወካይ የሆኑትን የግፍ እስረኛውን የአቶ ክርስቲያን ታደለን ያለመከሰስ መብት ሊያነሳ ነው።
አቶ ክርስቲያን ታደለ ፓርላማ የገቡት በአማራ ክልል ምዕራብ ጎጃም ዞን ቋሪት ምርጫ ክልል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)ን ወክለው ተወዳድረው ነው።
አቶ ክርስቲያን ፓርላማ ከገቡ በኋላ በምክር ቤቱ የመንግሥት ወጪ፣ አስተዳደር እና ቁጥጥር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ሆነዋል።
ነገር ግን በአማራ ላይ የታወጀውን ጦርነትና በህዝቡ ላይ እየተፈጸመ ያለውን ጭፍጨፋ በመቃወማቸው ላላፉት ሰባት ወራት በአዲስ አበባ እና በአዋሽ ሰባት ኪሎ በግፍ እስር እየተሰቃዩ ይገኛሉ፡፡
አቶ ክርስቲያን ለግፍ እስር ከተዳረጉ ከሰባት ወራት በኋላ ነው ፓርላማው ያለመከሰስ መብታቸውን ነገ የሚያነሳው።
ለፓርላማ አባላት የተላከው አጀንዳ የአንድ የምክር ቤት ያለመከሰስ መብት እንደሚነሳ ያትታል።
እንደ ምንጮች ከሆነ ያለመከሰስ መብታቸው የሚነሳው የምክር ቤት አባል አቶ ክርስቲያን ታደለ መሆናቸውን ገልጸዋል።
ከአቶ ክርስቲያን በተጨማሪ ሌላኛው የአብን ተወካይ ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔም ባለፈው ጥር መጨረሻ ላይ በቁጥጥር ስር መዋላቸው ይታወሳል።
ሆኖም ግን ምክር ቤቱ በአሁኑ ወቅት ያለመከሰስ መብት የሚያነሳው የአቶ ክርስቲያንን ብቻ ነው፡፡
እነ አብይ እንመራበታለን የሚሉት ሕገ መንግሥት፤ “ማንኛውም የምክር ቤት አባል ከባድ ወንጀል ሲፈጽም እጅ ከፍንጅ ካልተያዘ በስተቀር ያለ ምክር ቤቱ ፈቃድ አይያዝም፤ በወንጀልም አይከሰስም” ሲል ይደነግጋል።
ነገር ግን ምንም አይነት ወንጀል ሳይፈጽሙ የተገኙት እነ አቶ ክርስቲያን በውድቅት ሌሊት በጠገቡ የአገዛዙ ወታደሮች እየተደበደቡ ታስረዋል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion