የብልጽግና ዘመቻ

የብልጽግና ጦር በባህርዳር ዙሪያና በጎጃም አካባቢዎች ለፈጽመው ያሰበው ዘመቻ ተጋለጠ
ከሰሞኑ በጎጃም አገው ምድር ዳንግላ ሲካሄድ የነበረው ከባድ ውጊያ በአገዛዙ ጦር ሽንፈት እየተገባደደ ሲሆን ፣ ይህ የጨበጣ ቀጥሎ የብልጽግና ጦር ሸሽቶ ወጥቷል፡፡
የአገዛዙ ሃይል ሙትና ቁስለኛውን እንኳን መሰብሰብ ሳይችል ወደ ጫካ በመሸሽ ከባድ መሳሪያ ሲተኩስ እንደነበር ተረጋግጧል፡፡
በዚሁ በአገው ምድር  ጫራም ትናንት የተጀመረው ውጊያ አሁንም የቀጠለ ሲሆን ፋኖዎች ከአገዛዙ ጦር ጋር አንገት ላንገት ተናንቀዋል፡፡
ወደ አዲስ ቅዳም ገብቶ የነበረው የብርሃኑ ጁላ ጦርም የፋኖን ምትና የገበሬውን ዱላ መቋቋም አቅቶት አካባቢውን ለቆ ወጥቷል፡፡
በተጨማሪም በዚሁ በጎጃም ጢስ አባይ ትናንት ከባድ ውጊያ የተደረገ ሲሆን ጢስ አባይንም ፋኖ ቆጣጠሩ ታውቋል፡፡ ነገር ግን ከከተማዋ የወጣው ሃይል በስፍራው የአርሶ አደር ቤቶችን እያቃጠለ ፣ ንጹሃንን እየገደለ ፣ እናቶችን እየደፈረ ነው፡፡
እንዲሁ በባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ጭንባ አካባቢ በተካሄደ ውጊያ በአገዛዙ ሰራዊት ላይ እጅግ ከባድ የሚባል ሰብዓዊ ኪሳራ እንደደረሰበት የታወቀ ሲሆን፣ በህይወት የተረፈውም ተመልሶ ባህርዳር መኮድ ካምፕ ገብቷል።
ከሰብዓዊ ኪሳራው ባሻገርም 15 አባላቱ ጉዞ ላይ እያሉ ቀድመው በመክዳት ፋኖን መቀላቀላቸው ታውቋል። በሚከዱበት ወቅትም ወንዝ ሊወስዳቸው የነበረ ቢሆንም የአካባቢው ገበሬዎች አረጋግተውና እገዛ አድርጎላቸው ከእነመሳሪያቸው በሰላም ፋኖን ሊቀላቀሉ ችለዋል።
በሌላ በኩል ደግሞ በነበረው ውጊያ 13 የሰራዊቱ አባላት መማረካቸው ታውቋል።
ብልጽግና ከትናንት ጀምሮ በባህርዳር ዙሪያ ወረዳዎች ትንኮሳና ጥቃት የከፈተበት ምክንያት "አገዛዙ በተለይ በጭስ አባይ አካባቢ ጥቃት ሲፈፅም፣ ከደቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ ያለ የኃይል አጋርነት ስላሰጋው ነው" የሚል መረጃ ወጥቷል፡፡
በተጨማሪም ባህርዳር ለስብሰባ የመጡትን የአገዛዙን አመራሮችን ሽፋን ሰጥቶ ለማሳለፍ እቅድ ስላለው ወደ ትንኮሳና የከባድ መሳሪያ ድብደባ ገብቷል፡፡
ሌላው ደግሞ አገዛዙ "ጭስ አባይ ያለውን ኃይል ማዳከም ከቻልኩ፣ ለቀጣይ ስምሪቶቼ እንከን ይቀንስላቸዋል፤ የጭስ ዓባይ ፋኖ ባህርዳር ላይ ትኩረት ማድረጉን ይቀንሳል፤ ቀሪው ጎጃም ለሚደረገው ውጊያ ሽፋን እንዳያደርግ ማድረግ እችላለሁ" በሚል ስሌት መሆኑን የሚጠቁሙ መረጃዎች ወጥተዋል፡፡
አብይ አህመድ ወደ ባህርዳር ላሰበውን ጉዞ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠርም የሰሞኑ ጥቃቶች ምክንያት እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ አብይ ወደ ከተማዋ አዘናግቶ ሊገባ ማሰቡም ነው እየተነገረ ያለው፡፡
ሆኖም ሰሞንኛው የፋኖ እንቅስቃሴ ወደ ከተማዋ ሊያደርገው ያሰበውን እና ፋኖን አጥፍቻለሁ በሚል ላሰበው ፕሮፓጋንዳ እንዳልተመቸው ታውቋል፡፡
ለቀጣይ ጉዞው ለማመቻቸትም መጋቢት 7 በባህርዳር ዙሪያ ቀበሌዎች ጥቃት ለመሰንዘር የውጊያ ካርታ ተዘጋጅቷል።
በዘንዘልማ በር  አቅጣጫ ዘንዘልማ፣ጎንባት፣ ሮቢት፣ ወረብ፣ አቡነሐራ እና የሞሽት ናቸው።
በእነዚህ ቀበሌዎች የሚንቀሳቀሱ ፋኖዎችን መሀል አስገብቶ ለመምታት በደቡብ ጎንደር ደራ ወረዳ አዋሳኝ ቀበሌዎች በኩል ተመሳሳይ የሀይል ስምሪት ሰጥተው ጦር እያስጠጉ ነው።
ወንጀጣ-ጭንባ  መስመር በዚህ አካባቢ ከባህርዳር የመኮድ የሚነሳው ኃይል ጥቃት የሚፈጽምባቸው አካባቢዎች የወንጀጣ፣ወገልሳ፣ጭንባ፣ ከፊል የሰሜን ሜጫ፣ ሰሜንና ደቡብ አቸፈር ቀበሌዎች እና ጣና መለስ የሚገኙ ቀበሌዎችን ኢላማ ያደረገ ነው ተብሏል።
ከባህርዳር መኮድ ከሚያሰማሩት ኃይል በተጨማሪ በተመሳሳይ ሰዓት ከሊበን፣ቁንዝላ  እና መሸንቲ ተጨማሪ ኃይል አሰማርተው ከበባ ሊፈጽሙ አስበዋል ተብሏል፡፡
ትናትን ውጊያ የተጀመረባቸው ጭስ አባይና ገንጅ አካባቢዎችም የዚህ እቅድ አካል ናቸው፡፡
ጉብሪት-ቅንባባ- ብራቃት - መርዓዊ -መሸንቲ አካባቢዎችም ይ7እዚህ እቅድ አካል መሆናቸው የተነገረ ሲሆን ፣ ይህ ሁሉ እቅድ ደግሞ ወዲያውኑ በፋኖ እጅ መግባቱ ነው የተነገረው፡፡
በዚህም ፋኖ ለእነዚህ ዘመቻዎች ምላሽ ለመስጠት እየተዘጋጀ መሆኑ ታውቋል፡፡
በተመሳሳይ በትናንትናው እለት በደቡብ ወሎ ወግዲ ፣ ከላላና ገነቴ እንዲሁም ከደሴ በቅርብ ርቀት ላይ ባለው ተሁለደሬ ወረዳ ላይ ከባድ ውጊያ ሲካሄድ ውሏል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion