የአማራ ፋኖ በጎጃም

የአማራ ፋኖ በጎጃም ከፍተኛ ድል እያስመዘገበ ቢሆንም ህዝቡ ብዙ እንደሚጠብቅ ምክትል ሰብሳቢው ፋኖ አስረስ ማረ ገለፀ

የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢና የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊ ጠበቃና የህግ ባለሙያው ፋኖ አስረስ ማረ ዳምጤ የአማራ ፋኖ በጎጃም አመራሮች ከፋኖ ሰራዊት አባላት ጋር ባደረጉት ውይይት ንግግር አድርጓል።
ፋኖ አስረስ ባህርዳር ዙሪያ ለሚገኙት የሰራዊት አባላትና አመራሮች የአማራ ፋኖ በጎጃም ዳግም ከተቋቋመ በኋላ ከፍተኛ ድል እየተመዘገበ ቢሆንም በዚህ መመፃደቅ የለብንም ብሏል።
ህዝብ ከእኛ ብዙ ስለሚጠብቅ ዘላቂ ውጤት የሚያስገኝ እንቅስቃሴ ላይ ማተኮር አለብን ያለው የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊው የአገዛዙን ዕቅዶች ሁሉ ማክሸፍ እንደሚገባ አሳስቧል።
በሰሞኑ ዘመቻ የፋኖን ዋና ዋና አመራሮች ከመምታት አቅዶ የተንቀሳቀሰው የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ፈጣን መልሶ ማጥቃት እርምጃ ባይወሰድበት ኖሮ ውጤቱ የተለየ ይሆን እንደነበርም ፋኖ የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢው ጠቁሟል።
ብርሃኑ ጁላ ሰሞኑን ብዙ ነገር ለማስተባበል ሲንደፋደፍ የነበረው ፋኖ በሚወስደው እርምጃ ስለተደናገጠ መሆኑን የገለፀው ፋኖ አስረስ እያንዳንዷ እንቅስቃሴ ዋጋ አላት ሲል ለሰራዊቱ አባላት ምስጋናውን አቅርቧል።
"ዐቢይ አህመድ ሰሞኑን አዲስ አበባ ያሉ ዲፕሎማቶችን ሰብስቦ ባህርዳር ላይ ከማንሸራሸር አስቦ ነበር፣ ነገር ግን በራሳቸው የደህንነት ጥናት ስለሚንቀሳቀሱ እምቢ ብለውታል" ሲልም ሃላፊው የአገዛዙ የፕሮፓጋንዳ ዕቅድ መክሸፉን አመልክቷል።
ፋኖ አስረስ ከፋኖ ሰራዊት ብዙ ስለሚጠበቅ ጠንካራ ስራ እየሰራን ነው ሲልም አክሏል።



0 Comments

Login to join the discussion