የወሎ ፋኖዎች ተጋድሎ

የወሎ ፋኖዎች እርስ በርስ ተናበው የአገዛዙን ጦር እንቅስቃሴ ማስቆማቸውን ገለጹ
በወሎ ቤተ አምሃራ ግዛት ወንድ ሴቱ ፣ ወጣት አዛውንቱ የአገዛዙን ጦር ላለፉት ስምንት ወራት ከቁርጥ ቀን ልጆቹ ፋኖዎች ጋር ሆኖ ድባቅ እየመታ መውጪያ መግቢያ አሳጥቷል፡፡
የምስራቅ አማራ ፋኖ ቃል አቀባይ ፋኖ አበበ ፈንታው ለሮሃ እንደገለጸው በተላያየ አደረጃጀት ውስጥ ያሉ የወሎ ፋኖዎች በሃይቅና በአምባሰል አካባቢዎች ተናበው አገዛዙን እየተዋጉ ነው ብሏል፡፡
የብርሃኑ ጁላ ጦር ላለፉት ሁለት ቀናት በእነዚህ ቀጠናዎች በተካሄደው ትንቅንቅ ከባድ ኪሳራ ማስተናገዱ የታወቀ ሲሆን ፣ የአገዛዙ ጦርም ከእነቅስቃሴ ውጪ መሆኑን የፋኖ አመራሩ ተናግሯል፡፡
በተጨማሪም በዘመቻ ውባንተ ታላቅ ገድል እየሰሩ ያሉት የምስራቅ አማራ ፋኖዎች ፣ ለፋኖ መረጃ ትሰጣላችሁ በሚል የታሰሩ የአማራ ተወላጅ የመከላከያ አባላትን ማስፈታታቸውን ፋኖ አበበ ገልጿል፡፡
ፋኖ አበበ ለሮሃ በሰጡት ቃል እንዳስታወቁት በወሎ ምድር ሽንፈት የገጠመው ሃይል ሙስሊም ክርስቲያኑን በግፍ እየጨፈጨፈ ነው፡፡
በጾም ላይ ያሉ የእስልምና እና የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች በየቤተ እምነታቸው በዚህ ጨፍጫፊ ሃይል ተረሽነዋል ሲል ተናግሯል፡፡
የምስራቅ አማራ ፋኖ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው ለአማራ ህዝብ ባስተላለፈው መልዕክት " የአማራ ህዝብ በህዝባዊ እንቢተኝነት ጭምር ትግሉን እንዲቀላቀል" ጥሪ አቅርቧል፡፡
ለዚህም በቀጣይ ራሱን የቻለ ጥሪ እንደሚያደርጉ ነው ያስታወቀው፡፡ ይህ ጥሪ በመላው የአማራ ክልል አካባቢዎች እንደሚጠራም ገልጿል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion