የአማራ ፋኖ ተጋድሎ

በተለያዩ ግንባሮች ውጊያው ሲቀጥል ለፋኖ የሚደረገው ህዝባዊ ድጋፍ ተጠናክሯል
በአራቱም የአማራ ግዛት በርካታ ግንባሮች የህልውና ተጋድሎው ተጠናክሮ ሲቀጥል ከሀገር ውስጥ እስከ ባህር ማዶ ለፋኖ ሰራዊት እየተደረገ ያለው ሁለንተናዊ የህዝብ ድጋፍ የሚበረታታ መሆኑን የፋኖ አመራሮች ለሮሃ ተናግረዋል።
ከቀናት በፊት የአማራ ፋኖ በጎጃም ሰብሳቢ አርበኛ ዘመነ ካሴና የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝ አዛዥ ዋርካው ምሬ ወዳጆን ጨምሮ በርካታ የፋኖ አመራሮች ይፋዎ የድጋፍ ጥሪ ማቅረባቸውን ተከትሎ በአስቸኳይ ጊዜ ኮሚቴዎች አማካኝነት እንቅስቃሴዎች ተጀምረዋል።
ከዚህም በተጨማሪ በይፋ ፋኖን ያልተቀላቀሉ ወጣቶች በተለያዩ የአማራ ክልል የወረዳና የዞን ከተሞች በህቡዕ በመደራጀት የአስቸኳይ ጊዜ መረጃ ልውውጥና የፋኖ ድጋፍ መዋቅር መዘርጋታቸው ታውቋል።
በዚህ ለማወቅ አስቸጋሪ በሆነ አደረጃጀት ግራ የተጋቡ የአገዛዙ ካድሬ ሃላፊዎችም ወጣቶችን በተደጋጋሚ በመሰብሰብ በጥቅም ለመደለል ከፍተኛ ሙከራ እያደረጉ መሆኑን ሮሃ ከምንጮቿ ያሰባሰበቻቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ።
በዚህ ሁሉ ዘርፈ ብዙ የትግል ፍልሚያ መሃል ወታደራዊው የፋኖ ሰራዊት የጦርግንባር ተጋድሎም ከወሎ እስከ ጎጃም ከሸዋ እስከ ጎንደር በተለያዩ አውደ ውጊያዎች ቀጥሏል።
በርካታ የአገዛዙ ሰራዊት መካከለኛና ከፍተኛ የጦር መኮንኖች እየተበታተኑበትና እስከ ወዲያኛው እያሸለበቡት በሚገኘው የጎጃም ምድር አሁንም ትንቅንቁ ቀጥሏል።
በሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳ ራሱን እያታለለ ያለውና በጦር ግንባር በፋኖ ሰራዊት እየተመታ ያለው የብርሃኑ ጁላ ቡድን ስብስብ ከትናንት ጀምሮ በተካሄዱ ውጊያዎችም የሚተማመንባቸውን ቦታዎች ሳይቀር ለቆ ወጥቷል።
ኮማንድ ፖስት የሚለውን የአፈና ስልት የሚመሩና የሚያዙ የአገዛዙ የሰራዊት መኮንኖችን እስከ ወዲያኛው መሸኘት ለአማራ ፋኖ በጎጃም ተደጋጋሚ የሚባል ኦፕሬሽን ሆኗል ሲል አንድ በቢቸና ግንባር የተሰለፈ የፋኖ አመራር ለሮሃ ገልጿል።
ይሄው የፋኖ አመራር እንደገለፀው የዐቢይ ሰራዊት 59ኛ ክፍለ ጦር ከፍተኛ አዋጊ መኮንንና የቢቸና፣ ሸበል በረንታና የአካባቢው ቀጠና የአገዛዙ የኮማንድ ፖስት አዛዥ ነበረ የተባለ አንድ አመራር ተገድሏል።
ኮሎኔል ሸዋነህ ገበየሁ የተባለ ይህ የብርሃኑ ጁላ አሽከር በቅርብ ሳምንታት የተገደሉትን የአገዛዙን ጦር አመራሮች ጎራ ተቀላቅሏል ተብሏል።
ኮሎኔሉ ከአምስት ቀናት ገደማ በፊት ወይራ በምትባል ቀበሌ የበላይ ዘለቀ ብርጌድ በዐቢይ ጦር ላይ በወሰደው የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ተመትቶ ለህክምና ከተወሰደ በኋላ መሞቱን ነው የፋኖ አመራሩ የገለፀው።
በዚህም የአማራ ፋኖ በጎጃም ከኮሌኔል እስከ ብርጋዲየር ጀነራል ማዕረግ ድረስ ያሉ የብርሃኑ ጁላ ጦር አዛዦችን አፈር ማልሰቡን ቀጥሏል።
በሌላ በኩል በወሎ ወረዳዎች በርካታ የጦር ግንባሮች ቀላል የማይባል የአገዛዙ ጦር በወሎ ፋኖና የምስራቅ አማራ ፋኖ ዕዝ ጥምር ሰራዊት ተጋድሎ ሊበታተን ችሏል።
በተለይም በፋኖ የተያዙ አውራ መንገዶች የአገዛዙ ጦር የሚፈልገውን ያህል ሃይል እንዳይጨምር ስላደረገው ሽንፈትን ለመከናናብ ተገዷል ሲሉ የፋኖ አመራሮች ለሮሃ ተናግረዋል።

0 Comments

Login to join the discussion