የሸዋና የጎንደር ተጋድሎ

በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በተካሄደ ውጊያ ከፍተኛ የአገዛዙ የጦር አዛዥ መገደሉ ታወቀ
በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ውጊያ ብልጽግና ያላሰበው ፣ ያልጠበቀው ናዳ እየወረደበተ ነው፡፡ በየግዛቶቹም ከኮለኔል እስከ ጀነራል ማዕረግ ድረስ ያላቸውን አዛዦቹ በፋኖ ተገድለውበታል፡፡
በዚህም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በራሳ ቀጠና ከሰሞኑ በተካሄደ ውጊያ የአገዛዙ ኮለኔል የተገደለ ሲሆን ፣ በማዕከላዊ ጎንደርም በትናንትናው እለት ለአምስት ሰዓታት የዘለቀ ከባድ ውጊያ ተካሂዷል፡፡
በሸዋ ጠቅላይ ግዛት ከሸዋ ሮቢት በቅርብ ርቀት ራሳ ቀጠና አሻል ወይም መዲና ፣ ኩሬ በረትና አባይ አጥር በተባሉ አካባቢዎች ላይ ላለፉት ቀናት በተደረገ ትንቅንቅ አንድ ከፍተኛ ወታደራዊ አዛዥን ጨምሮ ከ30 በላይ ወታደሮች ሲደመሰሱ በርካቶች ደግሞ ተማርከዋል፡፡
ከሸዋ ሮቢትና ከደብረሲና ወደ ራሳ ቀጠና ከገባው ሃይል ጋር ከመጋቢት 20 ጀምሮ በተደረገ ውጊያ ድርብ ድል ማግኘታቸውንም በሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ የመሃመድ ቢሆነኝ ክፍለጦር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ ስንታየሁ ደመቀ ገልጿል፡፡
ከአራት ጊዜ በላይ በቀጠናው ሽምቅ ውጊያዎች መካሄዳቸውን እና አገዛዙም አስከፊ ሽንፈት እንደደረሰበት ገልጸዋል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ፋኖ በጎንደር ከአገዛዙ ሃይል ጋር በማዕከላዊ ጎንደር ጭልጋ ወረዳ ጫንድባ ከተማ ትናንት ረፋዱ ላይ የጀመረው ውጊያ ለአምስት ሰዓታት ቀጥሎ የአገዛዙ ጦር ከባድ ኪሳራ ማስተናገዱ ታውቋል፡፡
በዚህ ውጊያ 25 ወታደር ፣ 6 ሚሊሻና 3 ፖሊስ ተገድሏል፤ በርካታ የብልጽግና ጦርም ከድቶ ፋኖን እንዲቀላቀል ተደርጓል፡፡'
በማዕከላዊ ጎንደር የአጼዎቹ ክፍለጦር የይፋግ ብርጌድ የቀጥቅጥ ሻለቃ ሃላፊ እንደገለጹት በትናንቱ ውሎ ታላላቅ ጀብዶች ተፈጽመዋል፡፡
በዚህም ጫንድባ የተባለቸው ከተማም በፋኖ ቁጥጥር ስር መግባቷ ታውቋል፡፡ በብልጽግና መዋቅር ውስጥ የነበሩ አመራሮችም ከድተው ፋኖን እየተቀላቀሉ መሆኑ ተነግሯል፡፡


0 Comments

Login to join the discussion