ግዙፉ ክፍለጦር

የአማራ ፋኖ በጎጃም  "በላይ ዘለቀ " በሚል ስያሜ ግዙፍ ክፍለጦር መሰረተ

አደረጃጀቱን እያዘመነ የሚገኘው በአርበኛ ዘመነ ካሴ የሚመራው የአማራ ፋኖ በጎጃም  በክፍለ ጦር ፣በእዝ እና በኮር ደረጃ እየተዋቀረ ሲሆን አምስት ብርጌዶችን ያካተተ  ክፍለ ጦርም መጋቢት 22/2016 ዓ•ም መስርቷል።
በክፍለ ጦሩ የተካተቱት የሸበል በረንታው በላይ ዘለቀ ብርጌድ ፣የደጀኑ ዛምበራ ብርጌድ ፣የደባይ ጠላትግኑ ደባይ ጮቄ ብርጌድ ፣የእናርጅ እናውጋው ሶማ ብርጌድ እና የእነማዩ በላይ ብርጌድ ሲሆኑ አዲሱ የተመሰረተው ክፍለ ጦርም በላይ ዘለቀ ክፍለ ጦር የሚል ስያሜ ተሰጦታል።
በክፍለጦሩ ምስረታ ላይ የተገኙት የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢ እና የአማራ ፋኖ በጎጃም ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው ፣የአማራ ፋኖ በጎጃም  ምክትል ሰብሳቢና የፖለቲካ ጉዳይ ኃላፊ ጠበቃ እና አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ፤ የአማራ ፋኖ በጎጃም ፋይናንስ እና ሎጀስቲክ ኃላፊ ፋኖ ኢንጅነር ማንችሎት እሱባለው ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ መቶ ዐለቃ አበበ ሰውመሆን ፣የአማራ ፋኖ በጎጃም አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ ፋኖ እሸቱ ጌትነት እና የአማራ ፋኖ በጎጃም ፋይናንስና ሎጀስቲክ ምክትል ኃላፊ ፋኖ መንበሩ ጌታየ ሲሆኑ በክፍለ ጦሩ ምስረታ ላይ የተገኙት ከፍተኛ አመራሮች ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎችንም ሰጠዋል።
የበላይ ዘለቀ ክፍለጦርን እንዲመሩ የተመረጡ አመራሮችም  ወታደራዊ አዛዥ - ፋኖ መቶ አለቃ አዳነ ጤናው ፣ ም/አዛዥ - ፋኖ ሻምበል ሐይማኖት ጌታቸው፣ ዘመቻ መምሪያ ኃላፊ - ፋኖ 10 ዓለቃ ታሪኩ ፣ ክ/ጦር አስተዳደር -ፋኖ ትግስት ጫኔ ፣ ኦርዲናንስ ኃላፊ  -ፋኖ አለኸኝ ካሴ ፣ ሎጀስቲክ -ፋኖ ምስጋናው ይታየው ፣ ስልጠና መምሪያ -መቶ ዐለቃ ወዳለው አንዳርጌ፣ ፋይናንስ -ፋኖ ተመስገን  ገዳሙ ፣ ሰብሳቢ  -ፋኖ በላይነህ ዋልተንጉስ
፣ ምክትል ሰብሳቢ - ፋኖ ደምሰው ታመነ፣ ፅ/ቤት ኃላፊ - ፋኖ በላይነህ ደምስ ፣ አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ - ፋኖ አባይነህ ምህረቱ ፣ ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ-  አርበኛ ጥላሁን አበጀ ፣ ፖለቲካ ዘርፍ  - ፋኖ መምህር አዳንከኝ እያ ፣ ቀጠናዊ ትስስር - ኢንጂነር ተሾመ ለገሰ ፣ ፀጥታና ማሕበራዊ ጉዳይ - ፋኖ ቢያዝን በዜ መሆናቸው ታውቋል።

0 Comments

Login to join the discussion