የዋርካው ምላሽ ስለመቀሌው ህክምና
ዋርካው ምሬ ወዳጆ በአገር ውስጥና በውጭ ለሚገኙ አማራዎችና የአማራ ትግል ደጋፊዎች የሰብዓዊ ድጋፍ ጥሪ አቀረበ
አማራ መከራው ሲበዛ ፣ ህልውናው ሲጣስ ቀደመው የደረሱት የምስራቅ አማራ ፋኖ ጀግኖች አለም አቀፍ የድጋፍ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የአማራን ህዝብ ለመጨፍጨፍና አንገት ለማስደፋት የአገሪቱን ሃብት እያፈሰሰ ያለው የብልጽግና አገዛዝ ቀላል የማይባል ውድመት በህዝቡ ላይ እያደረሰ ነው፡፡
ስለሆነም ይህን የአገዛዙን የክፋት አካሄድ ለማስቆም በዱር በገደሉ እየታገሉ ያሉት የምስራቅ አማራ ፋኖዎች ለተጎዱ ወገኖች የሚውል አስቸኳይ የሰብአዊ ድጋፍ ጥሪ አድርገዋል፡፡
አለም አቀፍ የሰብዓዊ ድጋፍ ማሰባሰብ ሂደቱን አስመልክቶ ለሮሃ ቲቪ ማብራሪያ የሰጠው የምስራቅ አማራ ፋኖ አዛዡ ዋርካው ምሬ ወዳጆ ፣ " ያለንበት ወቅት ወሳኝና አስፈላጊ በመሆኑ ፣ ወሳኝ ሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልገናል" ብሏል፡፡
ዋርካው ምሬ ወዳጆ "በዋናነት ድጋፉ ለሰብዓዊነት ጭምር የሚውል ነው" ያለ ሲሆን ፣" በተለያዩ ዙሮች በተደረጉ ጦርነቶች የቆሰለና የተጎዳ ህዝብ ያለበት ቀጠና በመሆኑ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልገናል" ሲል አብራርቷል፡፡
"የአማራ ዲያስፖራ ፣ የአማራ ባለሃብቶች ፣ የአማራ ማህበራትና ህዝቡ በቻሉት መጠን ድጋፋቸውን ሊያሳዩን ይገባል" ሲልም ጥሪ አቅርቧል፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ የምስራቅ አማራ ፋኖ መሪው ዋርካው ምሬ ወዳጆ ከሰሞኑ ጉዳት ደርሶበት መቀሌ አይደር ሆስፒታል ህክምና ተከታትሏል የሚል መረጃ የተሰራጨ ሲሆን ሮሃም በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ እንዲሰጥ ጥያቄ አቅርባለች፡፡
በምላሹም "ከህወሃት ጋር አብሮ የሚሰራው ራሱ ብልጽግና እንጂ እኛ ፋኖዎች አይደለንም" ሲል አርበኛው አብራርቷል፡፡ ስለሆነም ጉዳት ደርሶበታል ህክምናውንም በመቀሌ ተካታትሏል የተባለውን መረጃ ሃሰት ሲል አስተባብሏል፡፡
የፋኖ አዛዡ አክሎም የአማራ ትግል ከፍ ያለ ደረጃ ላይ ደርሷል ያለ ሲሆን "አገዛዙ ለስድስት ጊዜ ተጨንቆና ተጠቦ ኦፕሬሽኖችን ቢያካሂድም አንዱም ሳይሳካለት ቀርቷል" ብሏል፡፡
ከእኛ በኩል የገደለውም ሆነ የማረከው ፋኖ የለም ሲልም ገልጿል፡፡
Login to join the discussion