የደቡብ ጎንደሩ ተጋድሎ
ደቡብ ጎንደርን ጨምሮ በአማራ ክልል እየተካሄዱ ያሉ ተጋድሎዎች እንደቀጠሉ ነው
በአማራ ክልል እየተካሄደ ያለው ውጊያ አገርሽቶ የቀጠለ ሲሆን ደቡብ ጎንደርና ወሎን ጨምሮ የተለያዩ የክልሉ ግዛቶች ታላቅ ተጋድሎ እያስተናገዱ ነው፡፡
በደቡብ ጎንደር ክምር ድንጋይ ትናንት ምሽት ሶስት ሰዓት አካባቢ በከተማዋ በሚገኘው በትምህርት ቤት መሽጎ በነበረው የብልጽግና ሃይል ላይ የደፈጣ ጥቃት በፋኖ መድረሱ የታወቀ ሲሆን ፣ የአገዛዙ ጦርም ከባድ ኪሳራ አስተናግዷል፡፡
በዚሁ ደቡብ ጎንደር በታች ጋይንት ሁለት የተለያዩ ስፍራዎች ላይ ውጊያ የተካሄደ ሲሆን ፣ ሳሊ ከተባለ ስፍራ እስከ አጋር ድረስ እንዲሁም ከላይ ጋይንት ሳሊ እስከ አጋር ድረስ ባሉ ቦታዎች በአርበኛ ከፊያለው ደሴ የሚመራው የፋኖ ሃይል የብልጽግናን ጦር አፈር ከድሜ አስበልቶታል፡፡
የአገዛዙ ጦር ሆድ አደር አድማ ብተና እና ሚሊሻን ይዞ ፋኖ ከፊያለው ደሴን ለመክበብ እንቅስቃሴ ቢያደርግም አናብስቶቹ የገብርዬ ልጆች አይቀጡ ቅጣት ቀጥተው መልሰውታል፡፡
በውጊያውም ከባባድ መሳሪያዎችን ጨምሮ በርካታ ተተኳሽ ፋኖዎች አግኝተዋል፡፡ ብልጽግና የክፉ ቀን ደራሹ የነበረውን አርበኛ ከፍያለው ደሴን ለመግደል በተደጋጋሚ ቢሞክርም የራሱን ወታደር ከማስጨረስ የዘለለ ነገር ሊያገኝ አልቻለም፡፡
ይህን አስመልክቶ ማብራሪያ የሰጠው የአማራ ፋኖ በጎንደር የዘመቻ መምሪያ ሃላፊና የገብርዬ ክፍለጦር አዛዥ ፋኖ ከፍያለው ደሴ የብልጽግና ጦር አይቀጡ ቅጣት መቀጣቱን ለኢትዮ 251 ተናግሯል፡፡
01፡27_05፡21
በላይ ጋይንት ሳሊ በመከላከያ ካምፕ ውስጥ በተፈጸመ የደፈጣ ጥቃትም በውስጡ የነበሩ የአገዛዙ ወታደሮችና አድማ ብተናዎች መደምሰሳቸው ነው የተነገረው፡፡
በተመሳሳይ በትናንትናው እለት በደቡብ ጎንደር ከደራ ወደ እስቴ በሚወስደው መንገድ ላይ በተፈጸመ የደፈጣ ጥቃት ከባድ ውጊያ መቀስቀሱ ታውቋል፡፡
ወደ እስቴ ገላውዲዎስ በሚወስደው የአድማ ብተና እና የመከለካያ አባላት የፈረቃ ለውጥ ለማድረግ ሰልፍ ሰርተው በሚጓዙበት ወቅት በተፈጸመ ጥቃት የአገዛዙ ጦር ከባድ ጉዳት አስተናግዷል፡፡
በዚህ በገላውዲዎስ ውጊያ እስከ ኮለኔል ድረስ ማዕረግ ያላቸው የአገዛዙ ጦር አዛዦች የተገደሉ ሲሆን ፣ ከ150 በላይ ተራ ወታደሮች ተገድለዋል፡፡
ይህ ቦታም አርበኛ ውባንተ አባተ የተሰዋበት በመሆኑ የሱ ደመ ተመልሶበታል ብለዋል የፋኖ አዛዦች፡፡
ይህ በእንዲህ እንዳለ በሰሜን ወሎ ትናንት ሌሊት በተለያዩ አካባቢዎች ማለትም በዶሮ ግብርና በአሚድ ወንዝ እንዲሁም ሮቢት ወንዝ አካባቢ በተፈጸመ የደፈጣ ጥቃት በርካታ የአገዛዙ ጦር መደምሰሱና መቁሰሉ ተነግሯል፡፡ በተጨማሪም በርካታ ከባድ መሳሪያዎችና ተተኳሾች ተማርከዋል፡፡ ይህን ጥቃት ተከትሎም የወልዲያ ሆስፒታል በቁስለኞች ተጥለቅልቋል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ በደቡብ ወሎ ዋና ከተማ በሆነችው ደሴ ሆስፒታል የሚገኙ ሃኪሞች ከአንድ ኮለኔል ሞት ጋር በተገናኘ መታፈናቸው ተሰምቷል፡፡
ከሰሞኑ በአምባሰል ሲካሄድ የነበረውን ተጋድሎ ተከትሎ የቆሰለ አንድ ኮለኔል ወደ ደሴ ሆስፒታል የገባ ሲሆን ፣ ዶክተሮቹ ከተወሰነ ህክምና በኋላ ሪፈር ወደ ጦር ሃይሎች ሆስፒታል ቢልኩም ጉዞ ላይ እያለ በደሴና በኮምቦልቻ መካከል ባለ ስፍራ ህይወቱ ያልፋል፡፡
ይህን ተከትሎ ወታደሮቹ ወደ ሆስፒታሉ ተመልሰው ፣ አንድ ሰውን ሆስፒታሉ በር ላይ ገድለው ፣ ሌሎቹን ሃኪሞች ወደሰፈሩበት አይጠየፍ አዳራሽ አፍነው መውሰዳቸዋል፡፡
በዚያም ከባድ ስቃይ እየደረሰባቸው መሆኑ ታውቋል፡፡
Login to join the discussion