በከፍተኛ ሁኔታ እየተደራጀ ያለው ሃይል !

የአማራ ፋኖ በጎጃም ከፍተኛ አመራሮቹ በተገኙበት ሳሙኤል አወቀ ክፍለጦርን አቋቋመ።
የአማራ ፋኖ በጎጃም ከፍተኛ አመራር ባወጣው አዲስ አደረጃጀት መሰረት የዓባይ ሸለቆ ብርጌድ ፣ ሳሙኤል አወቀ ብርጌድ እና ሰዴ ብርጌዶችን ያካተተ ክፍለጦር ተመስርቷል።
የአማራ ፋኖ በጎጃም ምክትል ሰብሳቢ እና የፖለቲካ ዘርፍ ሃላፊው አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ ፣ የድርጅቱ ምክትል ሰብሳቢና ወታደራዊ አዛዥ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረውንና የአደረጃጀት መምሪያ ሃላፊው አርበኛ እሸቱ ጌትነትን ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የክፍለጦሩ ምስረታ ተካሂዷል።
በዚህም የተመሰረተው ክፍለጦር ሳሙኤል አወቀ ክፍለጦር የሚል ስያሜ እንዲሰጠው በከፍተኛ አመራሮች በኩል ተወስኗል።
በመርሃግብሩ ላይ የተገኘው የጦር አዛዡ ሻለቃ ዝናቡ ልንገረው የክፍልጦር አመራርና ሰራዊት ትግሌን አደራ ብሎ የተሰዋውን ታጋይ ሳሙኤል አወቀን አደራ እንዲወጡ ጥብቅ መልእክት አስተላልፏል።
የተሸከምነውን ታሪካዊ ሃላፊነት መወጣት የሚያስችል ድርጅታዊ ቁመና መወለዱን እና ለመርህና ለአሰራር በመገዛት በሙሉ አቅሙ ከጎናችን የተሰለፈውን ሕዝብ ማክበር እንደሚገባ ያሳሰበው ደግሞ አርበኛ አስረስ ማረ ዳምጤ ነው።
አርበኛ እሸቱ ጌትነት በበኩሉ ትግል ያለሃሳብ፣ ሃሳብ ያለድርጅት፣ ድርጅት ያለመርህ፣ መርህ ያለ መሪ የትም መድረስ ስለማይችሉ እኒህን ሙሉ አሟልቶ መታገል ግዜው የሚጠይቀው የውዴታ ግዴታ መሆኑንና የትግሉን መሪዎች ማክበርና መጠበቅ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን አስታውሷል።
በመጨረሻም ከዚህ በፊት በሳሙኤል አወቀ ብርጌድ ይጠራ የነበረው የጎንቻና አካባቢው ፋኖ "ጎንቻ ብርጌድ" ተብሎ እንዲጠራ ተወስኗል።
በዚህም የአማራ ፋኖ በጎጃም የሳሙኤል አወቀ ክፍለ ጦር አመራሮች አስር አለቃ ደርሳቸው አትንኩት ሰብሳቢ ፣ ፋኖ አቤል መልካሙ ም/ሰብሳቢ፣ ፋኖ ይታያል ጌታ ፣ ጽ/ቤት ሃላፊ ፣መቶ አለቃ ይንገስ ብርሀኑ ወታደራዊ አዛዥ ፣ ፋኖ ዳዊት ገብሬ ምክትል ወታደርዊ አዛዥ ፣ መቶ አለቃ አያሌው ዘመቻ መምሪያ ሆነው ተመርጠዋል፡፡ ሌሎች አመራሮችም ይፋ ተደርገዋል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion