የአርበኛ ዘመነ ጥሪ
አርበኛ ዘመነ ካሴ ካሁን በኋላ የተናጠል የድጋፍ ዘመቻ አናካሂድም ሲል ስለ አንድነቱ ጉዞው ተናገረ
የአማራ ፋኖ በጎጃም በውጭ አስተባባሪዎቹ በኩል የሚያሰባስበውን ድጋፍ አስመልክቶ በሰጠው መግለጫ “ በዘላቂነት ስለሚደረገው የድጋፍ አሰባሰብ ሂደት ማብራሪያ ሰጥትቷል፡፡
እንዲሁም ከሰሞኑ በሰሜን አሜሪካ የአማራ ፋኖ በጎጃም በተቆጣጠራቸው አካባቢዎች ላለው ሰብዓዊ ቀውስ የሚውል ድጋፍ እያሰባሰበ መሆኑን እና የአሰባሰብ ሂደቱን በተመለከተም ዝርዝር መረጃ አውጥቷል፡፡
በመሆኑም ሰብዓዊ ድጋፍ አሰባሳቢ ሃይሉ ለተከታታይ ቀናት በአሜሪካ ሶስት ከተሞች ማለትም በአትላንታ ፣ በሚኒያ ፖሊስና በዳላስ እንደሚካሄድ ይፋ አድርጓል፡፡
ዘመነ አክሎም “የአማራ አንገቱ አንድ ነው ፣ ካልን ለአንድነቱ አንገታችንን መስጠት አለብን” ያለ ሲሆን ካሁን በኋላ በተናጠል ድጋፍ ለማሰባሰብ አንሞክርም ብሏል፡፡፡
ይህ የድጋፍ ማሰባሰብ ዘመቻም የመጨረሻው የተናጠል እንቅስቃሴ መሆን ይኖርበታል ሲል አርበኛው አስጠንቅቋል፡፡
Most Popular
ከእሁድ እስከ እሁድ
ከእሁድ እስከ እሁድ - የሲኖዶሱ መልዕክት ለጠቅላይ ሚንስትሩ - የኢትዮጵያኑ የድረሱልኝ ጥሪ - ኦነግ ሸኔና መንግስት ... @roha_tv
July 2, 2023, 5:20 p.m.
ከእሁድ እስከ እሁድ
Login to join the discussion