ተጠባቂው የማዕከላዊው የአማራ እዝ

የአማራ ፋኖዎች የህወሃትን የራያ ወረራ በሚመለከት አንድ የጋራ መግለጫ ሊያወጡ መሆኑን አሳወቁ
የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ ዋና አዛዥ ኮለኔል ፈንታው ሙሃባ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በሰጡት ማብራሪያ “ ፋኖ አቅሙ እየጨመረና  ትግሉም ከፍ እያለ ነው ብለዋል፡፡
ኮለኔሉ የህወሃትን ወረራ ፣ የአማራ ፋኖ አንድነትን ፣ የፋኖ ሃይሎችን ወቅታዊ አቋምና አቅም በሚመለከት ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
በመሆኑም ኮለኔል ፈንታው የአማራ ፋኖ ወደ አንድ አደረጃጀት እንዲመጣ እየተነጋገርን ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በአማራ ርስቶች ላይ ያላቸውን አቋም ይፋ አድርገዋል፡፡ ህወሃት የፈጸመውን ወረራ በሚመለከት ሁሉም የአማራ ፋኖ አደረጃጀት በዚህ ጉዳይ ላይ ወጥ አቋም ይዞ አንድ መግለጫ እንዲያወጣ ተወስኗል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አሁን ባለው ሁኔታ ብልጽግና እንደሚለው እየተዳከምን ሳይሆን ፣ ከምንግዜውም በላይ ተጠናክረን እየሰራን ነው ሲሉ ተደምጠዋል፡፡
አንድ የአማራ ማዕከላዊ እዝ እያቋቋምን ነው ሲሉም አዛዡ ተናግረዋል፡፡  ይህን አንድ ወጥ አደረጃጀት ለመመስረትም እየተንቀሳቀስን ነው ብለዋል፡፡
ከዚህም ባለፈ በየበረሃው እየተዋጋን ያለነውን ፋኖዎች ህዝቡ በገንዘብም ፣ በሃሳብም ሊደግፈን ይገባል ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ እንቅፋት እየሆነብን ያለው የፋይናንስ ችግር ስለሆነ በዚህ ዙሪያ ሰፊ ድጋፍ እንፈልጋለን ሲልም ተናግረዋል፡፡


0 Comments

Login to join the discussion