የፋኖ አዛዦቹ ስለ አንድነት

የፋኖ አዛዦች ወደ አንድ ጠቅላይ እዝ የመምጣት እንቅስቃሴያቸውን በይፋ እየገለጹ ነው
የአማራ ፋኖ ወደ አንድ ማዕከላዊ መምሪያ እየመጣ መሆኑን በሁሉም ግዛቶች ያሉ የፋኖ አዛዦች በአጽንኦት እየገለጹ መሆኑ ይታወቃል፡፡
የወሎ እዝ አዛዡ ኮለኔል ፈንታው ሙሃቤ ፣ የአማራ ፋኖ በጎጃም ሊቀመንበር አርበኛ ዘመነ ካሴ ፣ የምስራቅ አማራ ፋኖ መሪው ዋርካው ምሬ ወዳጆ ፣ የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ እዝ አዛዥ ሻለቃ መከታው ፣ የአማራ ፋኖ በጎንደር ሰብሳቢ አርበኛ ባዬ ቀናው  ከሰሞኑ አንድ የአማራ ፋኖ እዝ ለመመስረት እንቅስቃሴ እያደረጉ መሆኑን ሲገልጹ ተሰምተዋል፡፡
የአማራ ፋኖ በጎንደር እዝ  ዋና አዛዥ ሻለቃ ሃብቴ ወልዴ “በጎበዝ አላቃ የነበረውን የፋኖ አደረጃጀት “ ከሻለቃ ወደ ብርጌድ ፣ ከብርጌድ ወደ ክፍለጦር ፣ ከክፍለጦር ወደ እዝ አሳድገናል” ብሏል፡፡
አሁን ላይ ፋኖ የተሻለ አቅም ላይ ይገኛል ያለው የፋኖ አዛዡ በየአቅጣጫው ያለው የብልጽግና ጦር ብትንትኑ እየወጣ ነው ሲል ገልጿል፡፡
አክሎም ሁሉም የአማራ ፋኖ በጋራ አንድ ቤት ለመስራት ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጾ ለዚህም ንግግር እያደረጉ መሆኑን ገልጿል፡፡
አያይዞም ህወሃት የአማራ ግዛቶችን መውረሩን በሚመለከት በሰጠው አስተያየት “አማራ በሁሉም አቅጣጫ ተከቦ ባለበት ወቅት ወጣቱ ወደ ትግል ከመግባት ውጪ አማራጭ የለውም ብሏል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion