የፋኖ አንድነትና ድል

ወደ አንድ ዕዝ በመምጣት ብስራት ያሰሙት የጎንደር ፋኖዎች የአገዛዙን ጦር ከጥቅም ውጭ ሲያደርጉት ውለዋል
አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ከተበታተነ ሸማቂ ሃይል ስብስብ ወደ መደበኛ ወታደራዊ አደረጃጀት በማደግ በዕዝ፡ በክፍለ ጦር፤ በብርጌድና በሻለቃ እየተዋቀረ የመጣው የፋኖ ሰራዊት በአራቱም የአማራ ጠቅላይ ግዛቶች ጥቃቅን ልዩነቶችን እያጠበበ የአንድነትና የድል ግስጋሴውን አስቀጥሏል፡፡
ዛሬ ከመናገሻዋ ጎንደር አካባቢዎች የተሰማው የአንድነት ዜናም ትልቅ ተስፋን የፈነጠቀ ሆኗል፡፡
በጎንደር በተለያዩ አደረጃጀቶች ስር የነበሩት የአማራ ፋኖዎች ወደ አንድ ዕዝ መጥተዋል፡፡
የአማራ ፋኖ በጎንደር ወደ አንድ ዕዝ ለመሰባሰብ ንግግሮችን ሲያደርግ ሰንብቶ ዛሬ ስምምነቱ ፍፃሜዉን ማግኘቱ ለወዳጅ ብስራት ለጠላት ደግሞ መርዶን ይዟል፡፡
በስምምነቱ መሰረት አርበኛ መሳፍንት ተስፉ የጎንደር ዕዝ የበላይ ጠባቂ፣ አርበኛ ባዬ ቀናው የጎንደር ዕዝ የጦር አዛዥ፣ አርበኛ ሀብቴ ወልዴ የዐማራ ፋኖ በጎንደር መሪ፣ ኮሎኔል ታደሰ የዐማራ ፋኖ በጎንደር የጦር አዛዥ ወደ ስምምነቱ የመምጣታቸው ብስራት ተሰምቷል፡፡
ስምምነቱን ተከትሎ በአጭር ቀናት ውስጥ የጋራ የተዋሃደ አመራር ተመርጦ ይፋ እንደሚደረግም ሮሃ ከፋኖ አመራሮቹ አረጋግጣለች፡፡
ወደ አንድነት ዕዝ የመጡት የአማራ ፋኖ በጎንደር ሃይሎች ከስምምነቱ ጎን ለጎን በአገዛዙ ጦር ላይ የሚወስዱትን እርምጃ አጠናክረው ቀጥለዋል፡፡
የአማራ ፋኖ በጎንደር የአድዋ ክፍለ ጦርና የኦሜድላ ክፍለ ጦር የፋኖ ሰራዊት በቋራና አለፋ ወረዳዎች ከፍተኛ ድል ተቀናድጅተዋል፡፡
የአድዋ ክፍለ ጦር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አርበኛ ተስፋ ጌታሁን ለኤቢሲ በሰጠው ቃል ትናንት ከማለዳ እስከ እኩለ ቀን ድረስ እንዲሁም በዛሬው ዕለት ቀኑን ሙሉ በተለያዩ አውደ ውጊዎች የአገዛዙ ሃይል መበታተንና ከጥቅም ውጭ ማድረግ የቻለ በድል የታጀበ ውጊያ ተካሄዷል ብሏል፡፡
አርበኛ ተስፋ በጎንደር ግዛት የተለያዩ አካባቢዎች ያለውን ድል አስመልክቶ ተከታዩን ብሏል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion