አማራ ፋኖ ወሎ እዝ ጀብዶች

ታላቅ ውህደት የፈፀመው የአማራ ፋኖ ወሎ እዝ ወደ ራያ ቆቦ ከተማ መግባቱ ተሰማ
የምስራቅ አማራ ፋኖ እና የወሎ እዝ ጥምረት በፈጠሩ ማግስት የብልጽግናን ጦር የፈረካከሱ ታላላቅ ጀብዱዎችን እየተፈጸሙ ነው፡፡
ከወልዲያ እስከ ቆቦ ፣ ከመርሳ እስከ ወግዲ ከባድ ውጊያ እየተደረገ ሲሆን የብርሃኑ ጁላ ጦርም የወሎ ፋኖዎችን የህብረት ክንድ መቋቋም አቅቶት እየሸሸ ነው፡፡
ላለፉት ሶስት ቀናት በቀጠለው ጦርነት ድል በድል ሆኖ የቀጠለው የአማራ ፋኖ በወሎ እዝ ታላላቅ ከተሞችን ከብልፅግና ሰራዊት እያስለቀቀ መሆኑም እየተነገረ ነው።
በትናነትናው እለት ከጠዋቱ 11: 00 ጀምሮ አራዱምና ራያ ቆቦ ከተማን ከብልፅግናው አገዛዝ ለማስለቀቅ የተደረገው ትንቅንቅ በውጤት እየተቋጨ መስሏል።
በዛሬው እለት በቆቦ ከተማ እየተካሄደ ያለው ተጋድሎ የቀጠለ ሲሆን በርካታ የፋኖ ሃይልም ወደ ከተማዋ ገብቷል።
በአንፃሩ ደግሞ የብርሃኑ ጁላ ጦር ከተማዋን ለቆ እየወጣ መሆኑ እየተነገረ ነው።
ይህን ትነቅንቅ ተከትሎም በዛሬው እለት ከአዲስ አበባ መቀሌ የሚወስደው ዋና መንገድ ዝግ መሆኑ ታውቋል።
የአማራ ፋኖ በወሎ እዝ ከትናንት በስቲያ ጀምሮ በወልዲያ ዙሪያ ፣ በላስታ ፣ በደቡብ ወሎ ወግዲ አካባቢዎች ታላቅ ተጋድሎ እያደረገ ነው።
በዚህም ተዝቆ የማያለቅ ድል እያገኘ መሆኑን የፋኖ መሪዎቹ ጭምር እየተናገሩ ነው።
ይህ ያስደነገጠው የብልፅግና ጦርም የምስራቅ አማራ ፋኖን ዩኒፎርም የባህር ሃይል ወታደሮቹን በማልበስ በፋኖ ስም ለዝርፊያ ማሰማራቱን ዋርካው ምሬ ወዳጆ ተናግሯል።

0 Comments

Login to join the discussion