የጎንደር ፋኖዎች የጋራ ውጊያ

አንድ ለመሆን የአደረጃጀት ስራ ብቻ የቀራቸው የጎንደር ፋኖዎች ውጊያዎችን በጋራ እያደረጉ መሆኑን ገለጹ
በአራቱም አቅጣጫ ያሉ የአማራ ፋኖዎች በመካከላቸው ያለውን ልዩነት አጥብበው ለወጡለት ተመሳሳይ አላማ በጋራ ለመዋቀድ መማማልና መዋሃድ ከጀመሩ ሰነባብተዋል፡፡
በዚህም ጎጃም ፣ ጎንደርና ወሎ የአንድነት ቃል ኪዳናቸውን አስረዋል፡፡ ታዲያ ከሰሞኑ በልዩነቶቻቸው ላይ በመነጋገር መፍትሄ አበጅተው ወደ አንድ እዝ ለመምጣት የተስማሙት የጎንደር ፋኖዎች አሁን ላይ የአንድነት ጉዟቸው ተጠናቆ የአደረጃጀት ስራ ብቻ እየሰሩ መሆኑን አሳውቀዋል፡፡
የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና አዛዥ አርበኛ ባዬ ቀናው ውህደቱን አስመልክቶ ከኤቢሲ ጋር ባደረገው ቆይታ “ ውህደቱ እየተጠናቀቀ መጥቷል” ብሏል፡፡
መለያየቱ እንደማይበጅ አውቀን ወደ አንድ ለመምጣት ያደረግነው ጉዞ ተሳክቶ ወደመጨረሻው መጥቷል የሚለው አርበኛ ባዬ የአደረጃጀትና የመዋቅር ጉዳይ ብቻ ነው የሚቀረን ሲልም ገልጿል፡፡
አርበኛው አክሎም “ በአንድነትና በውህደት አገዛዙን አሸንፈናል” ያለ ሲሆን ፣ “ከሰሞኑም በተለያዩ አካባቢዎች ከሁሉም የጎንደር ፋኖዎች ጋር ተነጋግረን እና ተናበን በርካታ ቦታዎችን ነጻ አውጥተናል” ሲልም አስታውቋል፡፡ 


0 Comments

Login to join the discussion