ፋኖ እና የምክክር ኮሚሽኑ

ብልጽግና ባዘጋጀው የማደናገሪያ የምክክር ኮሚሽን ላይ በጭራሽ እንደማይገኝ ፋኖ አሳወቀ
በተሰማራበት የጦር ግንባር ሁሉ ድል ቀንቶት የማያውቀው የብልጽግናው አገዛዝ ፣ ስልጣኑን ለማቆየት ሲል የማይጠቀማቸው የማታለያ ስልቶች የሉም፡፡
ይህ ሃይል ያሸነፈ ሲመስለው ከማንም ጋር አልደራደርም ፣ አልነጋገርም የሚልና ስልጣኑ አደጋ ውስጥ የገባ ሲመስለው ደግሞ ለድርድርም ሆነ ለልመና ወደ ኋላ የማይል መሆኑ በተደጋጋሚ አሳይቷል፡፡
ታዲያ በዐቢይ አህመድ አሊ የሚመራው ይህ ሃይል ላለፉት ዘጠኝ ወራት በአማራ ክልል ከፋኖ ጋር እያደረገ ባለው ውጊያ ያልጠበቀውና ያላሰበው ሽንፈት ሲገጥመው በሽምግልና እንዲሁም በምክክር ኮሚሽን ሰበብ ስልጣኑን ለማቆየት እያለመ ነው፡፡
ብልጽግና በአራቱም የአማራ ግዛቶች ሽንፈት ሲገጥመው ፣ “ ችግራችንን በምክክር ኮሚሽን በኩል እንፍታ” በሚል ድለላ የራሱን ስልጣን ለማጽናት እየጣረ ነው፡፡
ለዚህም ቀለብ በሚሰፍርላቸውና እንዳሻው በሚቆጣጠራቸው የኮሚሽኑ ሰዎች በኩል “ለታጠቁ ሃይሎች” በሚል ጥሪ እያደረገ ነው፡፡
ይህንን በሚመለከት ምላሽ የሰጠው የአማራ ፋኖ በጎጃም የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ ማርሸት ጸሃው” ለእኛ ጥሪ አልተደረገም ፣ ቢደረግም አንሳተፍም” ሲል ለአሜሪካ ድምጽ ራዲዮ ተናግሯል፡፡
ፋኖ ማርሸት አክሎም “አገዛዙ አዳራሽ ተከራይቶለት ፣ ወጪውን ሸፍኖለት የሚንቀሳቀሰው ኮሚሽን ነው ላወያይ እያለ ያለው” ይላል፡፡
ቃል አቀባዩ አክሎም “የእኛ አላማ አገዛዙን አስወዶ ፍትህን ማንበር ነው” ያለ ሲሆን “ በጭራሽ ትግላችንን አቁመን በዚህ ኮሚሽን በሚዘጋጀው ውይይት ላይ አንገኝም” ሲል አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion