የፋኖ የአዲስ አበባ ጉዞ

“ወደ አዲስ አበባ ለማድርገው ጉዞ እየተዘጋጀሁ ነው” ያለው የሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ ፋኖ በቅርቡ አንድነታችንን እናበስራለን” አለ
አገዛዙ ራሱ በሚያስተዳድረውና በቀጠራቸው የማህበራዊ ሚዲያዎቹ በኩል ፋኖን አጥፍቻለሁ ፣ ክልሉንም ተቆጣጥሬያለሁ ማለት ከጀመረ ሰነባብቷል፡፡
ይሁን እንጂ ይህ የአገዛዙ ቡድን በባለስልጣናቱም ሆነ በጦር አዛዦቹ በኩል ይህን ቢለፍፍም ሃቁ ግን ከ80 በመቶ በላይ የሚሆነው የአማራ ክልል አካባቢ በፋኖ ቁጥጥር ስር መሆኑ ነው፡፡
በመሆኑም ከዕለት ወደ እለት ወታደሮቹ እየተደመሰሱበትና እየትማረኩበት ያለው ብልጽግና የፋኖን ክንድ መቋቋም ሲያቅተው ተራ ፕሮፓጋንዳ ላይ ተተምዷል፡፡
ይህን በሚመለከት ከአንክር ሚዲያ ጥያቄ የቀረበለት የአማራ ፋኖ ሸዋ ጠቅላይ ግዛት እዝ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ፋኖ አበበ ሙላቱ “ በሸዋ አካባቢዎች የብልጽግና ጦር ያለባቸው አካባቢዎች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው” ብሏል፡፡
በዚህም የብልጽግና ጦር ያለባቸውን ጥቂት ከተሞች ዘርዝሯል፡፡ ደብረብርሃን ፣ ሸዋ ሮቢት ፣ ጣርማበር ፣ ደብረሲና ፣ አለም ከተማ ፣ ሞላሌ ፣ ሚዳ መራኛ ፣ ዘመሮ እና እነዚህን መሰል ትንሽ ከተሞችን ነው የተቆጣጠረው ብሏል፡፡
ፋኖ አበበ አክሎም አደረጃጀታችንን አጠናክረናል ፣ አሁን ላይ ዞናችንን ተቆጣጥረን ወደ አዲስ አበባ ለመጓዝ ዝግጅት እያደረግን ነው ሲል ገልጿል፡፡
በተጨማሪም ይህን የአማራ ትግል ማንም ምድራዊ ሃይል አያስቆመውም ያለው ቃል አቀባዩ ፣ ይህንን ደግሞ ሆዳም አማራውም ሆነ አብይ መስማት አለባቸው ብሏል፡፡
አክሎም የፋኖን አንድነት በቅርቡ ለህዝባችን እናበስራለን ሲል ተድምጧል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion