የተመላሽ ተፈናቃዮች ምሬት

እነሽመልስ አብዲሳ ለፖለቲካ ፍጆታ በግዳጅ ወደ ኦሮሚያ የመለሷቸው ተፈናቃዮች የባሰ ችግር ውስጥ ነን አሉ

ባለፉት ዓመታት የኦነግ ታጣቂዎችና በሽመልስ አብዲሳ የሚመራው የኦሮሚያ ክልል ልዩኃይል በትብብር ያሳደዷቸውን አማራዎች ከቅርብ ወራት ወዲህ ወደ ቀያቸው እንመልሳለን በሚል እነሽመልስና አረጋ ከበደ የፖለቲካ ቁማር ጀምረው ነበር።

ተፈናቃዮችም ቀድሞውኑ ነፍሳችንን ለማትረፍ በሚል ጥለነው የመጣነው ቀያችን አሁንም አስተማማኝ ባለመሆኑ እዚሁ በረሃብ ብንሞት ይሻላል በሚል አቤቱታ የእነሽመልስን ሴራ ተቃውመው ነበር።

ያም ሆኖ "ቀያችሁ ሰላም ነው፣ ቤት ንብረታችሁ እንዳለ ነው፣ መደበኛ ህይወታችሁን ቀጥሉ" ተብለው ከደብረ ብርሃንና ሌሎች አካባቢዎች በግዳጅ ወደ ወለጋ የተወሰዱት አማራዎች ቃል የተገባው ሁሉ ውሸት መሆኑን አጋልጠዋል።

ከኦሮሚያ ክልል በመንግስት ሽፋን ይፈፀም የነበረን ግድያና ጥቃት ሸሽተው በአማራ ክልል ከቆዩ ተፈናቃዮች መካከል የተወሰኑት እነሽመልስና አረጋ ከበደ ባደረጉት ስምምነት ወደ ቀድሞ ቀያቸው ሊመለሱ ነው የተባለ ሰሞን የቀረበው ጥያቄ ሳይመለስ ቀርቷል።

ተፈናቃዮች ወደ ቦታቸው ከተመለሱ በኋላ ሁኔታዎች እንዳልተመቻቹላቸው ለጀርመን ድምፅ ሲናገሩ በተለይ የመኖሪያ ቤት ችግሮችና የግብርና ግብዓት አልተሟላም ብለዋል።

“መሬታችንም፣ ንብረታችንም እያገኘን አይደለም፣ ከመጣን ወደ ሶስት ወራት እያስቆጠርን ነው፣ መጠለያ ውስጥ ነው ያለነው" ሲሉም እነሽመልስ ያደረጉትን ማጭበርበር ኮንነዋል።

"የግብርና መሳሪያ ከመቆፈሪያ ጀምሮ አልተሰጠንም፣ የግብርና ግብዓትም አልቀረበልንም ዘርም፣ ምንም አቅርቦት የለም፣ በምዕራብ ወለጋ ቶሌ ነው የምንነኖረው፡፡ ” ሲሉም አክለዋል።

ሌላ በዚሁ በምዕራብ ወለጋ ዞን ቶሌ በተባለ አካባቢ በመጠለያ ጣቢያ እንደሚኖሩ የገለፁ ሌላ ተመላሽም በተመሳሳይ የግብርና ግብዓትም ሆነ የመኖሪያ ቤት ችግር እንዳለባቸው ገልፀዋል።

በደብረብርሐን መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃዮች ደግሞ ወደነበሩበት ቦታ ለመመለስ ምዝገባ እንዳደረጉና ፈቃደኛ ያልሆነ ተፈናቃይ ደግሞ እርዳታ እንደሚቋረትበት ተነግሮታል ብለዋል።

ከዚህ በፊት እንዲሄዱ ተመዝግበው ያልሄዱ ተፈናቃዮች እርዳታ ተቋርጦባቸዋልም ብለዋል፡፡

በደቡብ ወሎ ዞን ጃራ ቁጥር 1 የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ የሚገኙ ተፈናቃይ ደግሞ ወደ መጡበት ለመመለስና የግብርና ስራ ለመጀመር ቢፈልጉም “የሚሰማን አጣን” ብለዋል።

በያዝነው የክረምት ወቅት አምርተን በቀጣዩ ዓመት ራሳችን ለመቻል ፍላጎት ቢኖረንም ወደ ቦታችን የሚመልሰን አካል አልተገኘም ሲሉ ነው ቅሬታቸውን ያቀረቡት፡፡

የብልፅግና ሹመኞች የፖለቲካ ፍጆታ ለማግኘትና ተፈናቃየችን መልሰን እያቋቋምን ነው የሚል ሀሰተኛ ፕሮፓጋንዳን በሚዲያዎቻቸው ለማሰራጨት የተቻኮሉ ቢሆንም እውነታው ከእነእርሱ ቅጥፈት በተቃራኒ ሆኗል።

ውሸታቸው ሲጋለጥና ከፍተታቸው ሲነገር አፈና የሚቀናቸው የአገዛዙ አመራሮችም ተፈናቃዮችን ለመመለስ ብዙ ስራዎች እንደሚቀሩ ሲነገራቸው  እንደለመዱት "የኦሮሞ ጥላቻ አለባቸው" በሚል ጥበት ውስጥ ተወሽቀው ሰንብተዋል።

ያሻቸውን ፕሮፓጋንዳ ቢሰሩም ግን ራሱ ህዝቡ ማጋለጡን ቀጥሏል።

0 Comments

Login to join the discussion