የአማራ ክልሉ ተጋድሎ

ከፍተኛ ቁጥር ያለው የብልጽግና ሃይል በተደመሰሰባት የላሊበላ ከተማ ምንም ዓይነት እንቅስቃሴ አለመኖሩ ተገለጸ

በሰሜን ወሎ ዞን ላስታ ወረዳ ላሊበላ ከተማ በትናንትናው እለት ፋኖ ወደ ከተማዋ በመዝለቅ አውሮፕላን ማረፊያውን ጨምሮ የተለያዩ አካባቢዎችን በመያዝ በአገዛዙ ጦር ላይ ኦፕሬሽን መስራቱ ይታወቃል፡፡ ይህን ተከትሎም በዛሬው ማለዳ ሁሉም በየቤቱ ሆኖ ሁኔታውን እየተከታተለ ሲሆን ትላንት በነበረው ውጊያ ከተፋላሚ ኃይሎች ባሻገር መከላከያ በከባድ መሣሪያ ስድስት ንፁሐንን ገድሏል። 

ትላንት ከቀኑ 11:30 ገደማ የፋኖ ኃይሎች የቅዱስ ላሊበላ አየር ማረፊያን ከስድስት ሰዓታት ቁጥጥር በኋላ ለቀው ወጥተዋል።

በዚህም ከ87 በላይ የቡድንና የነፍስ ወከፍ መሣሪያዎችን የወሰዱ ሲሆን ዛሬ ማለዳ ወደ ቅዲስ ላሊበላ የአየር በረራ አለመኖሩም ተመላክቷል፡፡

በትላንትናው ውጊያ እስከ 70 የሚደርሱ የመንግሥት ኃይሎች ሙት ሲሆኑ በውል ቁጥራቸው ያልታወቀ ቁስለኛ ሆነዋል።

በሌላ በኩል በጉና በጌምድር ትላንት እኩለ ቀን ላይ እንደገና የተቀሰቀሰው ከባድ ውጊያ እስከ ሌሊቱ አጋማሽ ቀጥሎ አድሯል። 

በዚህ ከባድ ውጊያ የደረሰውን ዝርዝር ጉዳት ማወቅ አልተቻለም።

በምግብ ቤት ይመገቡ የነበሩ አራት ንፁሃን በአድማ ብተና የተገደሉ ሲሆን ፣ ከሁለት ቀናት በፊት በነበረው ውጊያ ከ45 በላይ የመንግስት ኃይሎች ላይ ጉዳት  መድረሱ ይታወሳል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ አካል የሆነው ቋራ ኦሜዳድ ክፍለጦር ቋራ ወረዳን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሯል። 

ክፍለጦሩ አዳሩን እልህ አስጨራሽ ውጊያ ሲያደርግ ያደረ ሲሆን በመጨረሻም ሶስት ካምፖችን መደምሰስ መቻሉን የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ቃል አቀባይ ለኢትዮ 251 ሚዲያ ገልጿል።

አሶል አካባቢ የሚገኝ የሚሊሻና የፀረ ሽምቅ ካምፕ፣ ሽመልእግር መውጫ የሚገኝ የአድማ ብተና ካምፕ እና አለሙ በር አካባቢ የሚገኝ የመከላከያ ኃይል ካምፕ ሙሉ በሙሉ የተመታ ሲሆን አድማ ብተና፣ ፀረሽምቅና ሚሊሻ እጅ የሰጠው እጅ ሰጥቶ የተረፈው ተደምስሷል ያለው ደግሞ የአማራ ፋኖ ጎንደር ዕዝ ቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር አዛዥ ፋኖ ሸጋ ጌታቸው ነው። 

የክፍለጦሩ አዛዥ እንደገለጸውም ራሱን የመከላከያ ኃይል ብሎ የሚጠራው  ቡድን ከተመታው እና ከተማረከው የተረፈው ካምፑን ጥሎ ወደ ሱዳን ገብቷል ብሏል፡፡

በአሁኑ ሰዓት ወደ ኢትዮጵያ አቅጣጫ ያለው መስመሩ የተቋረጠበት ሲሆን አልጣሽ ፓርክ ከመግባትና ወደ ጎረቤት ሱዳን ሀገር ከመሰደድ የዘለለ አማራጭ የለውም ብሏል። 

በነብስ አውጭኝ ሽሽት በከባድ መሳሪያ ከርቀት እየተኮሰ እየፈረጠጠ እንደሚገኝ እና ፋኖም እየተከተለ እያሳደደው እንደሆነ ሻለቃ ሸጋው ጌታቸው ተናግሯል፡፡

በተልዕኮው በቋራ ኦሜዳድ ክፍለጦር ስር የሚገኙ 100 አለቃ ደጀኔ ብርጌድ፣ ነብሮ ብርጌድ እና ዳግማዊ ቴውድሮስ ብርጌድ እየተሳተፋ ይገኛል ሲልም ገልጿል።

0 Comments

Login to join the discussion