የአማራ ክልል ውሎ

ህወሃት የአላማጣ ከተማን በወረረበት ወቅት በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ውጊያዎች እየተካሄዱ ነው
ብልጽግና በአማራ ክልል በራሱ ከፈጸመው ወረራ በተጨማሪ የአማራን ርስቶች በህወሃት በማስወረር ለአማራ ህዝብ ያለውን ጥላቻና ንቀት በይፋ አሳይቷል፡፡
በዚህም ላለፉት ወራት ሲፈጽመው የነበረውን ራያን የማስወረር ተግባር በዛሬው እለት አላማጣን በማስወረር የራያን ጉዳይ ጨርሻለሁ እያለ ነው፡፡
በቀጣይም እስከ ግንቦት 30 ጠለምትን፣ እስከ ሰኔ 30 ደግሞ ወልቃይትን ለህወሃት እንደሚያስረክብ ስምምነት ላይ ደርሷል፡፡
በመሆኑም ዐቢይ አህመድ ትናንት ማታ ዓላማጣ ከተማን ለህወሓት በይፋ አስረክቧል፡፡
የብልጽግናው ሰው ዐቢይ አህመድ አሊ ለህወህቱ ጌታቸው ረዳ ማስጠንቀቂያ ሰጥቶታል፡፡ እንደራያ ሁሉ ወልቃይትን መውሰድ ከፈለጋችሁ ታጣቂዎቻችሁ ወደ አላማጣ ሲገቡ ምንም አይነት ጭፈራና የደስታ ምልክት በከተማዋ ላይ እንዳያሰሙ በተጨማሪም በሚዲያው ላይ ነገሮችን አታራግቡ ብሎታል፡፡
በዚህም ህወሃቶች ተኩስም ሆነ ጭፈራ ሳያሰሙ ወደ ራያ አላማጣ ከተማ ሰተት ብለው  በሰልፍ ገብተዋል፡፡
የዐቢይን ቃል አክብረው የወልቃይትና የጠለምትን የወረራ ጊዜም አመቻችተዋል፡፡
ጌታቸው ረዳም እንደከዚህ ቀደሙ ሌሊት ስድስት ሰዓት ላይ በፌስቡክ ገጹ ላይ የስላቅ ጽሁፍ አስፍሯል፡፡ ታጣቂዎቻቸው ወደ አላማጣ በገቡበት ቀን ከአላማጣ ዙሪያ ሁለት ቀበሌዎች ላይ ታጣቂዎቻችን አስወጥተናል ሲል ገልጿል፡፡
ምናልባትም ጌታቸው ከአላማጣ ዙሪያ ያስወጧቸውን ታጣቂዎች ወደ ከተማው ማስገባታቸውን መግለጽ ፈልገው ይሆን የሚል አስተያየት እያሰጠ ነው፡፡
በመሆኑም የህወሓት ታጣቂዎች ሰልፍ ሰርተው በመግባት በሦስት በዓላማጣ ከተማ በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ሠፍረዋል። ዲሽቃና ሞርታር የመሣሠሉትን መሣሪያዎች አየር ማረፊያ እና ንብራ ትምህርት ቤት አጥምደዋል።

የዐማራ ብልጽግና ባይሆን ለይምሰል  መግለጫ ለማውጣት ይፈቀድልኝ ብሎ ዐቢይ አህመድን ደጅ እየጠና መሆኑም ተነግሯል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ ትናንት ግንቦት 16/2016 ዓ.ም ደሴ ከተማ 4ኛ ፖሊስ ጣቢያ የቦምብ ጥቃት ተፈጽሟል።
በተፈጸመው የቦምብ ጥቃት  ቢያንስ አራት የፖሊስ አባላት መሞታቸውን ምንጮች አረጋግጠዋል።
ሰሞኑ ደሴ ከተማ የሚገኘው ገራዶ ወታደራዊ ማዘዣ ጣቢያ በፋኖ ኃይሎች ተጠቅቶ በርካታ ጉዳት መድረሱ ይታወሳል።
በጎንደር ከተማ ዙሪያ በሰባት ቦታዎች ላይ ውጊያ እየተደረገ መሆኑ ታውቋል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion