የኢነግ ታጣቂዎች ጥቃት በደራ

የደራ ነዋሪዎች  በኦነግ ታጣቂዎች መከራና እንግልት እየደረሰብን ነው አሉ
በሰሜን ሸዋ የተለያዩ አካባቢዎች አጠቃላይ ብልጽግና ወለድ ችግር መኖሩ የሰነበተ ቢሆንም፣ የደራ ወረዳ ግን ከሁሉም የከፋና ማንነት ተኮር ጭፍጨፋው በስፋት የሚካሄድበት ነው፡፡በእነ ሽመልስ አብዲሳ የሚደገፈው ኦነግ ሸኔም የዚህ ማንነት ተኮር ጭፍጨፋ ተጠያቂ ነው፡፡
ይሁን እንጂ በአካባቢው ያለው ገበሬ ጥቃት ሲመረው የሚፈጽመውን መከላከል ፋኖ አጠቃ በሚል እንደሚያራግቡ ይነገራል፡፡
በተለይም በወረዳው ገጠራማ በሆኑት ሰረርኩላና ቱቲንን በመሳሰሉ ቀበሌዎች የሚኖሩ አማራዎች፣ እንደ ትምህርት እና ጤናን የመሳሰሉ ማኅበራዊ ግልጋሎቶችን ማግኘት ቅንጦት ሆኖብናል ሲሉ አስረድተዋል።
የአማራ እና የኦሮሞ ተወላጆች በስፋት በሰላም በኖሩባቸው ቀበሌዎች፣ በተለይም ካለፉት ሦስት ዓመታት ወዲህ በተደጋጋሚ ብሔር ተኮር ጥቃት ሲፈጸም ቆይቷል፡፡፡
በወረዳው እንደ ትምህርትና ጤና ያሉ አገልግሎት ሰጪ ተቋማት፣ በኦነግ ታጣቂዎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰባቸውና አብዛኞቹ አገልግሎት መስጠት አቁመዋል።
አብዛኞቹ ትምህርት ቤቶችም ዝግ መሆናቸውንና፣ የትምህርት አሰጣጥ ስርዓቱም ካለው  ችግር ጋር ተያይዞ የተቆራረጠና ተከታታይ ያልሆነ እንደሆነ የዞኑ ትምህርት መምሪያ አስረድቷል።
በተጨማሪ የታጠቁ የኦነግ ኃይሎች ከመኪና በማስወረድ ከገበያ ስፍራ፣ ከመኖሪያ ቤታቸው፣ ከሰርግ እና ለቅሶ ቦታዎች ንጹሃንን አፍኖ በመውሰድ “ይህን ያህል ብር አምጡና እንለቃችኋለን” የሚል ተደጋጋሚ ድርጊት እንደሚፈጸም ነዋሪዎች አስረድተዋል።

0 Comments

Login to join the discussion