የቆሰለው ጀነራል

የብልጽግና ጦር አመራሮች በስብሰባ ላይ ባሉበት ወቅት የቦምብ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ተገለጸ
የአማራ ፋኖ በጎንደር እዝ ያስተላለፈው የተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ገደብ መቀጠሉን የእዙ ቃል አቀባይ ፋኖ ያለው አዱኛ ተናግሯል፡፡ ፋኖ ያለው አክሎም በበለሳ መሽጎ የነበረው የብልጽግና ጦርም እርምጃ ተወስዶበታል፡፡
በዚህም እየሸሸ የነበረው የአገዛዙ ጦር በንጹሃን ላይ ጭፍጨፋ መፈጸሙን ቃል አቀባዩ ተናግሯል፡፡  በአርባያ በለሳ ያለው መከላከያ ፣ አድማ ብተና እና ሚሊሺ እንዲሁም ካድሬዎች እርምጃ እንደተወሰደባቸው የገለጸው የፋኖ አመራሩ በተለያዩ አካባቢዎችም ከ20 በላይ ንጹሃን ተጨፍጭፈዋል ብሏል፡፡
ቃል አቀባዩ በቋራ ግንባር በቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር ፋኖዎችና በአገዛዙ ጦር መካከል ከባድ ውጊያ እየተካሄደ ነው ያለ ሲሆን  በሽንፋ፣ በደለጎና በሉባባ አካባቢዎች ከባድ ተጋድሎ ተካሂዷል፡፡
ለተከታታይ አራት ቀናት በቀጠለው ውጊያ ደለጎ ፖሊስ ጣቢያ ተደምስሶ በርካታ የአገዛዙ ሃይል ተገድሏል፡፡
በቋራ ሉባባ በተሰኘ ቦታ ላይ የብልጽግና ጦር አመራሮች ጭምር በተሰበሰቡበት የቦምብ ጥቃትና ከፍተኛ ውጊያ ተከፍቶ እንዲደመሰሱ ተደርጓል ተብሏል፡፡ በዚህም አዳራሹ ውስጥ ያሉት ሁሉም የብልጽግና ሰዎች ተደምስሰዋል፡፡
በተመሳሳይ በእዙ ስር የሚገኘው የቋራ ኦሜድላ ክፍለጦር ዳግማዊ ቴዎድሮስ ብርጌድ ባዳረገው ውጊያ በቋራ ደለጎ አንድ የመከላከያ ጀነራል ተመትቶ መቁሰሉን የክፈለጦሩ አመራር ለኤቢሲ ተናግሯል፡፡
የ98ኛ ክፍለጦር መከበቧንም አመራሩ ገልጿል፡፡፡


0 Comments

Login to join the discussion