የወሎ ተጋድሎና ድል

በሰሜንና ደቡብ ወሎ በርካታ አካባቢዎች አኩሪ ድሎች መመዝገባቸውን የአማራ ፋኖ በወሎ ልጅ ኢያሱ ክፍለ ጦር አስታወቀ
በወሎ ጠቅላይ ግዛት ትናንት ከሌሊቱ ጀምሮ የፋኖ ሰራዊት አስደናቂ ጀብዱዎችን እየፈጸመ ይገኛል፡፡
የአማራ ፋኖ በወሎ ልጅ ኢያሱ ክፍለ ጦር ዋና አዛዥ ሻለቃ ደምሌ ወይም ጥንቅሹ የውጊያውን ዝርዝር ጉዳዮች አስመልክቶ ለሮሃ በስልክ በሰጠው ቃል በወሎ ግዛት ሰሜንና ደቡብ ወሎ ዞኖች በርካታ ወረዳዎችን ባካለለው ከባድ ውጊያ የተመዘገቡ ድሎችን ጠቅሷል፡፡
በደቡብ ወሎና ሰሜን ወሎ ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች በጣም አኩሪ ድሎች ተመስገበዋል ያለው የክፍለ ጦሩ አዛዥ በተደረገው እልህ እጨራሽ ተጋድሎ የፋኖ ሰራዊት በሰሜን ወሎ ውርጌሳና አካባቢውን ሙሉ በሙሉ መቆጣጠር መቻሉን አስታውቋል፡፡
በቀይ አፈርና አካባቢው በተደረገው ውጊያ የዐቢይ ጦር የመሸገበትን ካምፕ በማቃጠል ከጥቅም ውጭ ያደረገው የፋኖ ጦር የአገዛዙን ቡድን መግቢያ መውጫ አሳጥቶታል፡፡
በደቡብ ወሎ ግንባር ደግሞ በአምባሰል ወረዳ ውጫሌ ከተማ ፋኖ በወሰደው የማጥቃት እርምጃ የአገዙን ጦር መበታተኑን የክፍለ ጦሩ አዛዥ ፋኖ ደምሌ አስታውቋል፡፡
በአዋሳኝ አካባቢ በተለምዶ ሮቢት ተብሎ በሚጠራው ስፍራም ረዘም ያለ ውጊያ መካሄዱን የገለጸው አዛዡ የብርሃኑ ጁላ ሰራዊት ሃይል ሲያልቅበት በተደጋጋሚ እየጨመረ የነበረ ቢሆንም በመጨረሻ ሽንፈቱን ተከናንቦ ቁስለኛውንና አክስሬኑን ይዞ መሸሹን አብራርቷል፡፡
በውጊያው ላይ እንደእየሁኔታው የአማራ ፋኖ በወሎ የልጅ ኢያሱ ክፍለ ጦር አንደኛ፤ ሁለተኛ፤ አራተኛ እና ሶስተኛ ሻለቃዎች መሳተፋቸውን የገለጸው የክፍለ ጦሩ አዛዥ ፋኖን መቋቋም ያልቻሉት በቂ ስልጣና ያልወሰዱ በዕድሜ ትንሽ ልጆች የሚባሉ የአገዛዙ ወታደሮች እየረገፉ መሆኑን አመላክቷል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion