የሸዋው ተጋድሎና የብልጽግና ሽንፈት

በሸዋ ግዛቶች በተደረገ ውጊያ ከፍተኛ ኪሳራ የደረሰበት የአገዛዙ ጦር በሄሊኮፕተር አስከሬን እየሰበሰበ መሆኑ ተገለጸ

የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የአፄ ይኩኖአምላክ ክፍለጦር በአርበኛ ውባንተ ብርጌድ ስር የሚገኘው የአይሻ ሰይድ ሻለቃ በትናንትናው እለት የብልጽግናን ጦር እንቅስቃሴ እግር በእግር በመከታተል ከካራ ቆሬ ተጨማሪ ሀይል ይዞ ወደ አጣዬ ለመግባት የሞከረውን ሀይል ከቀኑ 4:00 ጀምሮ ሆራ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ላይ በወሰዱት ጥቃት ሙትና ቁስለኛ አድርገዋል፡፡

በዚህ ሽንፈት የተነሳም ወደ ተነሱበት ካራ ቆሬ ሲመለሱ የፋኖ ሃይሎች  በድጋሜ ከቀኑ 9:30 ላይ ቀርሳ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ በወሰዱት የደፈጣ የማጥቃት ውጊያ በድጋሜ ሌላ ሽንፈትን አስተናግዶ አጣዬን በሩቅ እያዬ ወደ መጣበት ተመልሷል” ሲል የእዙ ምክትል የህዝብ ግንኙነት ንጋቱ ይታገሱ ለሮሃ ተናግሯል።

ያሰበው ያልተሳካለት የአገዛዙ ጦር በተለመደ የበቀል እርምጃው በእረኝነት ስራ ላይ የነበሩ ንፁሀን ህፃናትን ገድሏል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ የአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ በከሰም ክፍለጦር ስር የሚገኘው የሀይለማርያም ማሞ ብርጌድ የሃገረ ማሪያም ወረዳ  መዲና በሆነችው ሾላ ገበያ ከተማ መሽጎ በሚገኘው የአገዛዙ ጦር ላይ በተለያዩ አቅጣጫዎች የማጥቃት ኦፕሬሽን በመውሰድ መውጪያ መግቢያ አሳጥተውታል ሲል የህዝብ ግንኙነቱ ለሮሃ ተናግሯል።

ትናንት ሰኔ 11/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 2:00 ጀምሮ በደብረፅጌ ቀበሌ ቴክኒክና ሙያ ኮሌጅ ፣ወላድ አካባቢ ቁና ተራራ ተብሎ በሚጠራ ልዩ ስፍራ እንዲሁም ጥጎር በር በሚባል ስፍራ የተደራጀ ማጥቃት የፈፀመው የሀይለማርያም ማሞ ብርጌድ ሞርተር እና ዲሽቃ ይዞ  የሚገኘውን የብልፅግና ጦር  ክላሽና ስናይፐር ብቻ በመጠቀም እንደ ቅጠል እያረገፉት ነው ሲልም አክሏል፡፡

በሌላ በኩል የአገዛዙ ጦር የግሼራቤል ወረዳን ለመያዝ ሰኔ 8/2016 ዓም በዙ_23፣ሞርተርና ዲሽቃ ታጅቦ ከመሀል ሜዳ ከተማ በመነሳት ወደ ግሼራቤል ወረዳ ቢያመራም ወዠድ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ላይ በአማራ ፋኖ ሸዋ ዕዝ የአፄ ይኩኖ አምላክ ክፍለጦር የተለያዩ ብርጌዶች በቆረጣ የውጊያ ስልት  በደረሰበት የተደራጀ ጥቃት ራቤል ከተማን መያዝ ሳይችል ቀርቷል፡፡

የአፄ ይኩኖአምላክ ክፍለጦር የተለያዩ ብርጌዶች ባደረጉት የሶስት ቀናት ውጊያ የብርሀኑ ጁላ ጦር ሙትና ቁስለኛ ሆኖ በሔሊኮፕተር እየተለቀመ በመነሳት ላይ ይገኛል ሲል ፋኖ ንጋቱ ተናግሯል። 


0 Comments

Login to join the discussion