የትግራይ ጀነራሎች አደገኛ አካሄድ

በትግራይ የህወሃት ጀነራሎች ተሳትፈውበታል የተባለው የኮንትሮባንድ ስራ ጉዳይ እያነጋገረ ነው

በትግራይ ክልል የታጠቁ ኃይሎች እና ጄኔራሎች እንዲሁም የውጭ ዜጎች የሚሳተፉበት የወርቅ ሕገወጥ ቁፋሮና ኮንትሮባንድ እንደተጧጧፈ መረጃዎች እየወጡ ነው፡፡
በተለይ እንዳባጉና ወረዳ የሚገኘው የትግራይ ጀኔራሎች የሚቆጣጠሩት "ራህዋ" የወርቅ ማውጫ ከፍተኛ ሕገወጥ የወርቅ ቁፋሮና ኮንትሮባንድ እንደሚካሄድበትና ተዋናዮቹ የቀድሞ የሕወሃት ተዋጊዎች፣ ወጣቶች፣ ስደተኞችና ቻይናዊያን እንደኾኑ ሪፖርተር ዘግቧል።
ዘገባው፣ በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በ"ሒንጻት" የወርቅ ማውጫ ከኹለት ወራት በፊት በቀድሞ የሕወሃት ታጣቂዎችና በጥበቃዎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት 22 ሰዎች እንደሞቱ መስማቱን ገልጧል።
ሕገወጡ ወርቅ ወደ አዲስ አበባ፣ አሥመራ፣ ሐርጌሳ፣ ናይሮቢ እና ካምፓላ እንደሚሸጥና ከዚያም መዳረሻው ዱባይ እንደኾነ ምንጮች ስለመናገራቸው በዘገባው ላይ ተጠቅሷል።
ይን በሚመለከት ማብራሪያ የሰጡት የህወሃት ታጣቂዎች መሪና የአቶ ጌታቸው ምክትል ሌፍተናንት ጀነራል ታደሰ ወረደ "ሕገወጥ የማዕድን ማውጣት ስራው... አደገኛ ኬሚካሎች ጭምር የሚጠቀሙበት ነው፣ ቀጣይ ትውልድ ጭምር ወደ አደጋ የሚያስገባ ነው" ብለዋል፡፡
የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር በሕገወጥ ማዕድን ምዝበራ፣ ሰብአዊ እርዳታ መሸጥ እና ሌሎች የህዝብ ሀብት ስርቆት ተሳትፎ ያላቸው አካላት መያዝ መጀመሩን አስታውቋል።
አስተዳደሩ በሕገወጥ ተግባራቱ ተሳትፎ ያላቸው የመንግስት ባለስልጣናት ይሁኑ ወታደራዊ መሪዎች አልያም ባለሀብቶች ለሕግ እንደሚቀርቡ ገልጿል።
በትግራይ በተለይም በጦርነቱ እና ከጦርነቱ በኃላ ባሉ ግዜያት በስፋት እየታዩ ናቸው ተብለው ከሚገለፁ ሕገወጥ ተግባራት መካከል በሕገወጥ መንገድ ወርቅን ጨምሮ የተለያዩ ማዕድናት አውጥቶ፣ ለሕገወጥ ገበያ አቅርቦ መሸጥ አንዱ መሆኑ ይገለፃል።
በዚህ ተግባር የመንግስት ባለስልጣናት፣ ወታደራዊ አዛዦች እና የውጭ ሀገራት ዜጎች ጭምር እየተሳተፉበት እንደሆነ ይነገራል።
የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት ጀነራል ታደሰ ወረደ "ሕገወጥ የማዕድን ማውጣት ስራው፥ ኤክስካቫተር እና ሌሎች ተጠቅሞ በተለያዩ ቦታዎች የሚደረግ ቁፋሮ ነው። አደገኛ ኬሚካሎች ጭምር የሚጠቀሙበት፣ ቀጣይ ትውልድ ጭምር ወደ አደጋ የሚያስገባ ሆኖእያለ፥ ማዕድኑ ከየት ወደየት ይንቀሳቀሳል የሚል ደግሞ፥ ከዚህ ጋር የተሳሰሩ በርካታ ትልልቅ ወንጀሎች የሚፈፀሙበት ነው" ብለዋል።
ከዚህ የማዕድንና ምዝበራ በዘለለ በትግራይ በጦርነቱ ወቅት የወደሙ ተሽከርካሪዎች እና ከባባድ ወታደራዊ መሳሪያዎች እንዲሁም ሌሎች በከፍተኛ ዋጋ የሚገመቱ ብረታብረት የመንግስት ባለስልጣናት እና ወታደራዊ አመራሮች ጭምር በሚሳተፉበት የዝርፍያ ሰንሰለት የተሸጡበት ሁኔታ እንዳለም ዶቼ ቬለ ዘግቧል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion