የዐቢይ ትዕዛዝና የተቀየረው መጋረጃ

ዐቢይ አህመድ የፓርላማ አባላቱ ቤት ገብተው ያስተላለፉት መልዕክት እያነጋገረ ነው

ኑሮ ከብዷቸው በ14 ዓመታቸው ኢህአዴግን በተዋጊነት የተቀላቀሉት የበሻሻው ሰው ዐቢይ አህመድ አሊ ዛሬ የመንበረ መንግስቱን በክፉ የታሪክ አጋጣሚ በመቆጣጠራቸው ያንን ክፍ የልጅነት ዘመናቸውን እየተበቀሉት ይመስላሉ፡፡
ይሁን እንጂ ሰውዬው ዛሬ ላይ እየተበቀሉ ያሉት ድህነትን ሳይሆን ደሃን መሆኑ ደግሞ አሳዛዥኑ ክስተት ሆኗል፡፡ በድህነት ማቀው ባደጉባት ሃገር በሁሉም አቅጣጫ የሚያዩትን ደሃ ህዝብ በማሳደድና ግላዊ ምቾትን ለደሃው ህዝብ በማሳየት ላይ ተጠምደዋል፡፡
በሩቅ ያለውን ደሃ ገበሬ  በደሮን እና በድሽቃ እየጨፈጨፉ ፣ ስራቸው ያለውን አዲስ አበቤ ደግሞ ቤቱን አፍርሰው ሜዳ እየበተኑ ነው፡፡
በምትኩ እርሳቸውና ባለቤታቸው ሳይክል የሚነዱበትን እና ወክ የሚያደርጉበትን እንዲሁም እነ አዳነች አቤቤ በየሚዲያው ሰራነው እያሉ የሚመጻደቁበትን ፓርክ ሰርተዋል፡፡
ታዲያ ከሰሞኑ እኒህ ሰው ከመስቀል አደባባይ በደንበል ወደ ቦሌ ኤርፖርት በሚወስደው የቦሌ ጎዳና ላይ በምሽት ወክ ሲያደርጉ የፓርላማ አባላት መኖሪያ ቤት ጋር ይደርሳሉ፡፡
ዐቢይ ከጋሻ ጃግሬዎቻቸው ጋር ወክ እያደረጉ ባለበት ወቅትም የፓርላማ አባሉትን ቤት መጋረጃ በድንገት ይመለከታሉ፡፡
በዚህን ጊዜም የቆዩና የተለያዩ ቀለሞች ያላቸውን መጋረጃዎች በማየታቸው በቀጥታ የፓርላማ አባላቱን ቤት እያንኳኩ በማንቋሸሽና በመሳደብ “እንዴት የብልጽግና የፓርላማ አባል ሆናችሁ እንዲህ አይነት መጋረጃ ይኖራችኋል? ካሁን በኋላ ሁላችሁም አንድ አይነት ነጭ መጋረጃ ቀይሩ” በሚል ትዕዛዝ ሰጥተው ወጥተዋል፡፡
በቀጣይም መጋረጃው መቀየሩን ለመመልከት ተመልሰው እንደሄዱና በተለያየ ዲዛይን እና ቀለም የተመለከቷቸውን አምፖሎች እንዲቀይሩ አዘው ሄደዋል፡፡
የአምፖሉን መቀየር ለመመልከት መመለሳቸውን ባናረጋግጥም የፓርላማ አባላቱ ግን አለቃቸው ያዘዟቸውን ትዕዛዝ ለመፈጸም ከመርካቶ እስከ ኡራኤል መጋረጃና አምፖል ፍለጋ ሲንከላወሱ እንደነበርና ትዕዛዛቸውንም እንደፈጸሙ ተሰምቷል፡፡
ዐቢይ አህመድ በመሰረቱት የብልጽግና ፓርቲ ውስጥ በድርጅቱ አምኖ ለመታገልና ለመሰዋት ጭምር የሚንቀሳቀስ አባል የሌላቸው ፣ የድርጅቱ ርዕዮት የገባውና የተረዳ ተከታይ ያላፈሩ በአንጻሩ በሆድ አደርና  በአሸርጋጅ የተሞላ ፓርቲ ነው ያላቸው፡፡
በመሆኑም እርሳቸውም ፍላጎታቸውን በግድ ለማስፈጸም ይጥራሉ አባላቶቻቸውም የርሳቸውን ፍላጎት ፈጽመው መኖርን ቀዳሚ ተግባራቸው አድርገዋል፡፡ ይህም ለአይናቸው ቀለም ያልጣማቸውን መጋረጃና አምፖል በየቤቱ እየገቡ እስከማስቀየር አድርሷቸዋል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion