እየፈረሰ ያለው የብልጽግና መዋቅር

በአራቱም አቅጣጫ የተከበበችው ባህርዳር በውስጧ ያለው የብልጽግና መዋቅር እየፈረሰ መሆኑ ተነገረ

የአማራ ክልሏ መዲና ባህርዳር ለአገዛዙ ጦርም ሆነ ለእነ አረጋ ከበደ ቡድን እንደማዕከልነት እያገለገለች ያለች ከተማ መሆኗ ይታወቃል፡፡
ከተማዋ ላለፉት ጊዜያት በተደጋጋሚ በፋኖ ሃይሎች ተከባለች ፣ ፋኖዎችም ወደ ውስጧ ዘልቀው በመግባት በአገዛዙ ጦር ላይ ጥቃት ፈጽመዋል፡፡
ታዲያ አሁን ላይ ከተማዋ በአማራ ፋኖ በጎጃምና በአማራ ፋኖ በጎንደር በአራቱም አቅጣጫ ከበባ ተፈጽሞባታል፡፡
እንዲሁም በከተማዋ ያለው የአገዛዙ መዋቅር በከፍተኛ ሁኔታ እየፈረሰ መሆኑም በነዋሪዎች ጭምር እየተነገረ ነው፡፡

በሌላ በኩል አይበገሬዎቹ የተከዜ ክ/ጦር ክንደ ነበልባሎች ሰቲት ሁመራ ላይ የሥርዓቱን ጥምር ጦር እንደ ላም እየነዱት ይገኛሉ ሲል የአማራ ፋኖ በጎንደር ዋና አዛዥ አርበኛ ባዬ ቀናው ለሮሃ በላከው መረጃ አሳውቋል፡፡
የአማራ ፋኖ በጎንደር፣ ተከዜ ክ/ጦር፣ ጎይቶም ርስቀይ ብርጌድ በተሠራው መብረቃዊ ኦፕሬሽን በሥርዓቱ ጥምር ጦር ላይ የማያዳግም እርምጃ ተወስዷልም ብሏል።
ትናንት ነሐሴ 01/2016 ዓ.ም ሰቲት ሑመራ ዞን፣ አውራ ወረዳ ዙሪያ የሚንቀሳቀሰው ጎይቶም ርስቀይ ብርጌድ አውራ ወረዳን ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሩ ሥር አድርጓል። የአማራ ፋኖ በጎንደር፣ ተከዜ ክ/ጦር ወታደራዊ እቅድ አማካይነት በተደረገው ዓውደ ውጊያ በርካታ የመከላከያ ሠራዊት እስከወዲያኛው ሲሸኝ፣ 94 የሚሊሻ አባላት ከነመሣሪያቸው ፋኖን ተቀላቅለዋል።
ከዚህ በተጨማሪም 34 የነፍስ ወከፍ መሣሪያ፣ 2500 ተተኳሽ ጥይትና 2 ክላሽ መትረጊስ ከአገዛዙ ጦር  በምርኮ ተገኝቷል።
በተመሳሳይ በሻለቃ አንተነህ ድረስ የሚመራው አርበኞች ክፍለጦር በአርማጭሆና ዙሪያው የአገዛዙን ጦር እያርበደበደው ይገኛል።
ሶረቃና ዙሪያውን ከትናንት 9 ሰአት  ጀሞሮ  የተቆጣጠረው ይህ ክፍለ ጦር በስሩ ያሉት የጦሩ አባሎች በሽመል ማርከው የታጠቁት የአርማጭሆ አናብስቶች እንደ አባቶቻቸው በጀግንነት አንገት ላንገት እየተናነቁ ነው ።
ከትናንት 9 ሰአት ጀምሮ እስካሁኗ ሰአት ድረስ ውጊያው እንደቀጠለ ነው።የአገዛዙ ሃይልም ያለ የሌለ ሀይሉን አንቀሳቅሶ ከባድ መሳሪያ እየተኮሰ ለማምለጥ ቢሞክርም የአርማጭሆ ፋኖዎች እና አርበኞች አላንቀሳቅስ ብለውታል፡፡

0 Comments

Login to join the discussion